በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእርግዝና መከላከያ አቅርቦት ተደራሽነት በኮቪድ ምክንያት ተስተጓጉሏል - ተመድ


የጤና ባለሞያዎች የኮቪድ ክትባት ያገኙ ግለሰብን፤ ከክትባት በኋላ ክትትል ሲያደርጉ - በሰንዌይ የህክምና ማዕከል ማሊዥያ
የጤና ባለሞያዎች የኮቪድ ክትባት ያገኙ ግለሰብን፤ ከክትባት በኋላ ክትትል ሲያደርጉ - በሰንዌይ የህክምና ማዕከል ማሊዥያ

ኮቪድ-19 ዓለምን ካዳረሰ ወዲህ በ115 ሃገሮች የእርግዝና መከላከያ አቅርቦት ተደራሽነት መስተጓጎሉን ተመድ አስታወቀ።

የመንግሥታቱ ድርጅት የስነ ህዝብ ፈንድ ዋና ስራ አስኪያጅ ናታሊያ ካኒም በሰጡት መግለጫ ወረርሽኞች ሆኖ ሊሎች ቀውሶች ባሉበት ጊዜም ቢሆን እርግዝና መከሰቱ የሚቀር ነገር አይደለም።

ስለዚህ ሴቶች የሚያስፈልጋቸው መከላከያ እና ሌላውም የእናቶች እና ህጻናት ጤና መድሃኒቶች ሳይቋረጡ ሊቀርቡላቸው ይገባል ብለዋል።

ኮቪድ-19 ዓለምን ባዳረሰበት ዓመት በ115 ሃገሮች አስራ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች በአማካይ ለሦስት ወር ተኩል ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ግብዓት ሳያገኙ እንደቀሩ ድርጅቱ ገልጿል።

በዚህም የተነሳ 1ነጥብ አራት ሚሊዮን ያለፍላጎት ጽንሶች መፈጠራቸውን ዩኤንኤፍፒኤ በሪፖርቲ አመልክቷል።

ከኮቪድ-19 በተያያዘ የዩናይትድ ስቴትስ ዜና የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ህዝቡ ክትባቱን እንዲወስድ ለማበረታት በተዘጋጁ የቪዲዮ ማስታወቂያዎች እያተሳተፉ ናቸው።

የቀድሞ ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ ከባለቤታቸው ሎራ ቡሽ ጋር ሆነው የቀረቡ ሲሆን" ሸሚዛችንን ወደላይ ሰቅሰቅ አድርገን የሚገባንን እናድርግ" ብለዋል።

አብረዋቸው በማስታወቂያው ከነባለቤቶቻቸው የቀረቡት ባራክ ኦባማ ቢል ክሊንተን እና ጂሚ ካርተርም እንዲሁ እንከተብ ሲሉ አበረታትተዋል።

XS
SM
MD
LG