በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፍ ተቋማት እያንጸባረቁት ያለው አቋም ለኢትዮጵያ ምን ትርጉም አለው?


ዶ/ር መሰንበት አሰፋ አቶ ዩሃንስ አብርሃ
ዶ/ር መሰንበት አሰፋ አቶ ዩሃንስ አብርሃ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት በክልሉ ውስጥ የተከሰተውንቀውስ አስመልክቶ እያንፀባረቁት ያለው አቋም ምን ትርጉም አለው? የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢትዮጵያመንግሥታት ምልልስ፣ትግራይ ውስጥ አሁን ያለው ሁኔታና የሰብዓዊ ረድኤት አቅርቦት እንዲሁም የሰብዓዊመብቶች ጥሰቶች ላይ የተደረገ ውይይት ነው።

ዓለም አቀፍ ተቋማት እያንጸባረቁት ያለው አቋም ለኢትዮጵያ ምን ትርጉም አለው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:37:28 0:00


እንግዶቻችን

ዶ/ር መሰንበት አሰፋ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የቀበሉት ከፕሪቶሪያ ዩኒቨርስቲ የሰብዓዊ መብት ማዕከል ፤በሰብዓዊ መብት እና ዴሞክራሲ በአፍሪካ ነው። በሚዲያ እና ሐሳብን በመግለፅ ነፃነት ዙሪያ ሠርተው በናሽናል ዩኒቨርስቲ ኦፍ አየርላንድ ጎልዌይ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።

ዶ/ር መሰንበት ከዚህቀደም በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የሰብዓዊ መብት ክፍል ዳይሬክተር ነበሩ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርቲ የሕግ ትምሕርትቤት ኃላፊ እና ተባባሪ ዲን ሆነው ሠርተዋል። ዶ/ር መሰንበት አሰፋ አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግትምሕርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። በተጨማሪም ብሄራዊ የሕግ ማሻሻያ ኮሚቴ አባል ናቸው።

አቶ ዩሃንስ አብርሃ በአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ በንግድ አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።ከዚያም ፓሪስ ከሚገኘው የሶርቦን ዩኒቨርስቲ በፕሮጀክት ማነጂመንት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።ቤልጂየም ከሚገኘው አንትወርፐን ዩኒቨርስቲ ደግሞ የልማታዊ የመንግሥት አስተዳደር በማጥናትተጨማሪ ሁለተኛ ዲግሪ ተቀብለዋል።

አቶ ዩሃንስ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ በአዲስ አበባ፣ በፓሪስ፣ በብራስልስ ውስጥ ለ19 ዓመታት ሠርተዋል። እስከ መጋቢት 2012 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ውስጥ የደቡብእና የምዕራብ አውሮፓ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። አቶ ዩሃንስ በአሁኑ ሰዓት በካናዳ የሚገኙ ሲሆን፤የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን በመወከል በውጭ አገር እንቅስቃሴ የሚያደርግ ኮሚቴ ጋር አብረውበመሥራት ላይ ይገኛሉ።

(የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

XS
SM
MD
LG