በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሃጫሉን እኛ አልገደልነውም”- ጃል መሮ


"ጫካ ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሠራ ሽፍታ ቡድን - የገደልኩት እኔ ነኝ ብሎ እንዲያምን አይጠብቅም” - አቶ ታዬ ደንዳአ

  • "ጫካ ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሠራ ሽፍታ ቡድን - የገደልኩት እኔ ነኝ ብሎ እንዲያምን አይጠብቅም” - አቶ ታዬ ደንዳአ
“ሃጫሉን እኛ አልገደልነውም”- ጃል መሮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:35:23 0:00

በቅፅል ስሙ (ጃል መሮ) በሚል መጠሪያ የሚታወቀው በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኘው የኦሮሞ ነፃነትሠራዊት የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን አዛዥ አቶ ኩምሳ ድሪባ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያም ሆነኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂ እንዳልሆነ ገለፀ።ጃል መሮ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበረው ቆይታ ድምፃዊ ሀጫሉ ሥልጣን ላይ ካሉት መሪዎች ይልቅለኦሮሞ ነፃነት ጦር የቀረበ እንደነበር ገልፆ “ተቃውሞ ቢኖረው እንኳን እርሱን ልንገል የምንችልበትአንድም ምክኒያት የለም” - ብሏል።

አያይዞም፤ “መሳሪያ ከታጠቀው ሃይል ጋር ጦርነት ላይ ብንሆንም፤ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ግን በፍፁም ጥቃትአናደርስም” - ብሏል። ሰላማዊ ዜጎችን ከጥቃት የመከላከል ተግባር ደግሞ የመንግስት ነው ብሏል።

የ50 ዓመቱ የኦሮሞ ነፃነነት ጦር መሪ ኩምሳ ድሪባ ላልፉት ሁለት ዓመታ ምዕራብ ኦሮሚያን እንደሚመራ ተናግሯል። በደቡብ፣ በምዕራብ በሰሜን እና በአዲስ አበባ እንደሚንቀሳቀሱና ሰራዊቱ የማይንቀሳቀስበትቦታ እንደሌለ ገልጿል። በየቦታው የየራሱ የሆነ የጦር ቀጠና የየራሳቸው የጦር መሪ እንዳላቸውምገልጿል።

ጦሩ ከዚህ ቀደም ከ50 ዓመት በላይ በትጥቅ ትግል ውስጥ የነበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግበሰላማዊ መንገድ ወደ ሃገር ውስጥ ሲገባ፤ የኦሮሞ ትግል አልተቋጨም ብሎ ስለሚያምን በጫካ ቀርቶከኢትዮጵያ መንግሥት ወታደር ጋር በመዋጋት ላይ መሆኑን ተናግሯል።

“የኦሮሞ ነፃንት ጦር ሃጫሉን አይገለውም። በሃጫሉ ጉዳይ ላይ እጃችን የለበትም።” ካለ በኋላ ሃጫሉየእኛ ደጋፊ ነብር ብሏል። ሃጫሉ ሁንዴሳ ደጋፊያቸው እንዳልነበር ሕይወቱ ከማለፉ በፊት በሰጠው ቃለምልልስ ላይ ተናግሯል። ኩምሳ ለዚህ ቃለ ምልልስ ሲጠሰጥ፤ “ሃጫሉ ብቻ ሳይሆን አሁን በእስር ላይየሚገኙት በቀለ ገርባ እና ጃዋር መሐመድም የእኛ ደጋፊዎች አልነበሩም እንደውም የእኛን ሰራዊትትጥቅ አስፈትተዋል። የእኛን ስልት የሚቃወሙ ሰዎች አሉ። እነኛን ገደልናቸው ታዲያ? እኛ የምንታገለውነፃና ዲሞክራሲያዊት የሆነች ሰዎች ሐሳባቸውን በነፃነት መግለፅ የሚችሉበት አገር ለመመስረት ነው።ስለዚህ ሰዎች ስለተናገሩ አንገድልም። በሃጫሉ ግድያ ተጠያቂው መንግሥት ነው።” ሲል ተናግሯል።

በምዕራብ ኦሮሚያ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በእነዚህ ታጣቂዎች ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸውን፣በተለይ እነርሱ ወዳሉበት ቦታ ጥቆማ ሰጥተው መርተዋል ብለው የሚያስቡት ሰዎች ላይ በአሰቃቂ ሁኔታግድያን እንደሚፈፅሙ። በአጠቃላይ በሰው ልጆች ላይ ይህ ነው የማይባል አሰቃቂ ድርጊትን የሚፈፅሙመሆናቸውን በመግለፅ መንግሥት አካባቢው ላይ ወታደር በማሰማራት ጥበቃ ሲያደር እንደነበር በተለያየጊዜ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል። ድሪባ ኩምሳ፤ የትጥቅ ትግል ማካሄዳቸው ከመንግስት ወታደሮች ጋርጦርነት መግጠማቸውን ገልፆ ነገር ግን በሰላማዊ ዜጎች ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት እንደማያደርሱአስተባብሏል።

በቅርቡ ሕይወቱ ያለፈውን ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በተፈፀመ ጥቃትበመንግሥት የታመነ 166 ሰላማዊ ዜጎች እና 11 የፀጥታ አካላት አረጋግጠዋል። ግድያዎቹ እጅግ አሰቃቂበሆነ መንገድ መፈፀማቸውንና ጥቃቱም ብሔርን እና ኃይማኖትን መሰረት ያደረገ እንደነበር ከጥቃቱየተረፉ ተናግረዋል። 239 ሰዎች ደግሞ አካላቸው ጎድሏል። በተጨማሪም እስካሁን ግምቱ በትክክልያልታወቀ በ40 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ድርጅቶች፣የግለሰቦች መኖሪያ ቤት ተቃጥለዋል። ንብረት ወድሟል። ብዛት ያላቸው ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀውተሰደዋል። በቤተክርስቲያን እና ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተጠልለዋል። ካነጋገርናቸው ሰዎች መካከልአንዳንዶቹ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በአካባቢው ነዋሪ ወጣቶች እንደሆነ ሲናገሩ አንዳንዶቹ ደግሞበማያውቋቸውና በሰለጠኑ አልሞ ተኳሾች ጥቃት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ደግሞ በዚህ ድርጊት ውስጥ በጫካ የሚገኘው የኦሮሞ ነፃነት እጁ እንዳለበት ገልፀዋል። ድሪባ ኩምሳ ሰዎች በመገደላቸው የሰው ንብረት በመውደሙማዘኑን ገልጾ በዚህ ሰላማዊ ዜጎች ላይ በደረሰው ጥቃት ውስጥ በየትኛውም መልኩ እጃቸውእንደሌለበትና። “ዜጎችን ከደቦ መከላከል ደግሞ ሕዝቡን አስተዳድራለሁ የሚመው መንግስት ሃላፊነትነው” ብሏል።

በአጠቃላይ የኦሮሞ ጥያቄ እስኪፈታ እና ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት እስኪወርድ ትግላችንንእንቀጥላለን ብሏል። በሌላ በኩል “ጫካ ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሠራ ሽፍታ ቡድን - የገደልኩት እኔ ነኝ ብሎ እንዲያምን አይጠብቅም” ሲሉ የኦሮሚያ ብልፅግና ፖርቲ አቶ ታዬ ደንዳ ለአሜሪካድምጽ ገልፀዋል። ከዚህ ቀደምም በምዕራብ ኦሮሚያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የፈፀሟቸውን አሰቃቂወንጀሎች ማኅበረሰቡ እያወቃቸው እነርሱ ግን አልፈፀምን ብለው አስተባብለዋል ብለዋል።

(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

XS
SM
MD
LG