በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሥራቸውን ለቀቁ


በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ - ዋሽንግተን ዲሲ
በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ - ዋሽንግተን ዲሲ

በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት የነበሩት አቶ ብርሃነ ኪዳነ ማርያም በፈቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸው ተገለጸ።

በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ሚሽን ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ብርሃነ ሥራቸውን የለቀቁበት ምክንያት በትግራይ ክልል የቀጠለው ግጭት ነው ሲሉ መጥቀሳቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ባወጣው ዘገባ አመልክቷል።

አቶ ብርሃነ ኪዳነ ማርያም "ስራዬን የምለቅቀው በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ጦርነት እና መንግሥት በሌሎችም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚያደርሰውን ጭቆናና ውድመት ተቃውሜ ነው" ሲሉ ትናንት ባወጡት ግልጽ ደብዳቤ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ጠቅሷል።

አቶ ብርሃነ ኪዳነ ማርያም እኤአ በ2018 ከሦስት ዓመታት ገደማ በፊት እስከተባረሩበት ጊዜ ድረስ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እንደነበሩ ዜናው ጨምሮ አውስቷል።

XS
SM
MD
LG