በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት ስለትግራይ የሰጠው መግለጫ


የትግራዩን የህግ የበላይነት ዘመቻ ቀሪ ሁለት ዓላማዎች ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። ሁለቱ ዓላማዎች ደግሞ ሰብአዊ ድጋፍ መድረሱን ማረጋገጥና ክልሉን መልሶ መገንባት እንደዚሁም አሁንም በክልሉ ውስጥ በንቃት የሚንቀሳቀሱ ወንጀል ፈፃሚዎችን ለሕግ ማቅረብ መሆናቸውን አመልክቷል። የሕግ የበላይነት ዘመቻውን ለማዳከም የታቀዱ ማናቸውንም ወገንተኛ ጣልቃ ገብነቶች እና የፖለቲካ ዘመቻዎችን ግን ኢትዮጵያ አትቀበልም ብሏል የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መግለጫ።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያን መንግሥት ሕግ የማስከበር ሃላፊነት የዘነጉ ይመስላል ያሉ አንድ የዘርፉ ታዋቂ ምሁር በበኩላቸው ይህ በማንኛውም ሃገር በጥርጣሬ የሚታይ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ እንዳሉት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እየወጡ ያሉ መግለጫዎች በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረቱ አይደሉም።

"የቀራቸው የፌዴራል መንግሥቱ ወታደሮች ይውጡ ማለት ብቻ ነው” በማለት ነው የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ እይታ የተቹት። የተለያየ ደረጃ ያላቸው የተሳሳቱ መረጃዎች እንዳሉና ጫናዎች እንደሚደረጉም ጠቁመዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ስለትግራይ የሰጠው መግለጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:05 0:00
የኢትዮጵያ መንግሥት ስለትግራይ የሰጠው መግለጫ - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:28 0:00



XS
SM
MD
LG