በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደንና ኬንያታ ተወያዩ


ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኬንያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነቷን በኢትዮጵያ እና በሱዳን የሚካሄዱ ግጭቶችን ለማስቆም እንድትጠቅመበት የሚፈልጉ መሆናቸው ተገለጸ።

ፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደሩን ከተረከቡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በስልክ ኦፊሴላዊ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ከኬንያ ጋር ያላትን ዘላቂ አጋርነት አረጋግጠውላቸዋል።

ኬንያ የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት አባልነትዋን ለቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ትኩረት ሰጥታ ለመስራት እንድትጠቀምበት ፕሬዚዳንት ባይደን አሳስበዋል።

ሁለቱ መሪዎች በተለይም የአፍሪካ ቀንድን በሚመለከቱ ጉዳዮች ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ቃል መገባባታቸውን የስልክ ውይይታቸውን አስመልክቶ ከዋይት ሃውስ የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG