በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለኮቪድ-19 ክትባት አዲስ ጥናት


በፋይዘር እና ባዩንቴክ ህብረት የተሰራው የኮቪድ-19 ክትባት፣ እየተከተቡ ባሉ ሰዎች ላይ ቀደም ብሎ በሙከራው ወቅት ያስመዘገበውን ዓይነት ውጤታማነት እያሳየ መሆኑን አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ።

የእስራኤል ክሌሊት የምርምር ተቋም ተመራማሪዎች ባካሄዱት አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ያሳተፈ ጥናት እንደገለጠው ሁለት ጊዜ የሚሰጠው የፋይዘር ክትባት በማናቸውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች በቫይረሱ የህመም ስሜት በሚያመጣ ደረጃ እንዳይጠቁ በማድረግ ረገድ 94 ከመቶ ውጤታማነት አሳይቷል። አንዷን ብቻ ክትባት ለወሰዱ ሰዎች፤ 57 ከመቶ ቫይረሱን የመከላከል ዓቅም ሰጥቷቸዋል።

በአቻ ተመራማሪዎች ተገምግሞ በኒው ኢንግላንድ የህክምና መጽሄት ላይ የወጣው ይህ የእስራኤሉ ጥናት በሃገር አቀፍ የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር ላይ ያተኮረ ግምገማ ሲካሄድ የመጀመሪያ መሆኑ ነው።

ፋይዘር እና ባዮንቲክ ኩባኒያዎች የሰሩት ክትባት ላይ የተካሄደው ብዛት ያላቸው ሰዎች ያሳተፈ ሙከራ ዘጠና አምስት ከመቶ ውጤታማነት ማሳየቱን አስታውቀው እንደነበር የሚታወስ ነው።

XS
SM
MD
LG