በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በኮቪድ 19 ምክንያት ወደ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጉ የስራ ዕድሎች መክነዋል”


ወጣቶች በስራ ላይ ፣ ሀዋሳ ኢንደስትሪ መንደር (ፋይል)
ወጣቶች በስራ ላይ ፣ ሀዋሳ ኢንደስትሪ መንደር (ፋይል)

ከኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር ከሰባ በመቶ በላይ የሚሸፍኑት ወጣቶች መሆናቸውን የስነ-ህዝብ መዛግብት ያሳያሉ። ከእነዚህ ወጣቶች መካካል ለአቅመ-ስራ የደረሱትን ለእንጀራ ለማብቃት የወጠነው የሀገሪቱ መንግስት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን አቋቁሟል።

በአሁኑ ጊዜ ተቋሙን የሚመሩት አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንደሚናገሩት ኮሚሽኑ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን አዳዲስ የስራ መስኮችን የሚከፍቱ ዘርፎች እንዲበረክቱ፣የስራ ዕድሎች እንዲበዙ ጥረት እያደረገ ይገኛል።በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር 2013 ውስጥ 3 ሚሊየን የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ያቀደው ተቋሙ በተለይ የግብርናውን መስክ አቅም በማጤን በዘርፉ በርካታ የስራ ዕድሎች እንዲፈጠሩ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

ይሁንና ዛሬም ድረስ ስራን የሚመለከቱ ተግዳሮቶች መፈጠራቸው አልቀረም። ዓለምአቀፉ የኮሮና ቫይረስ ጫና ፣ስራ ፈጣሪዎችን የሚፈትን ቢሮክራሲ ፣ አስፈላጊ የፋይናንስ ድጋፍ እና በቂ የሙያ ስልጠና መርሀ-ግብሮች እጥረት ወጣቶች ከሚጠቅሷቸው ችግሮች መካከል ናቸው። ዕድል ቀንቷቸው በሀገሪቱ ውስጥ እየተበራከቱ በሚገኙት የኢንደስትሪ መንደሮች ውስጥ ለመቀጠር የበቁ ወጣቶችም በሚከፈላቸው ደሞዝ አናሳነት ምክንያት በስራቸው ላይ ሳይከራርሙ ይለቃሉ።

የሚያስተዳድሩት ኮሚሽን የተጠቀሱት ችግሮችን እንደሚረዳ የሚናገሩት አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣ እልባት ለማግኘት ከአጋር ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

ስለ ተቋማቸው ሰሞነኛ ተግባራት ብሎም በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ማብራሪያ ያዳምጡ።

“በኮቪድ 19 ምክንያት ወደ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጉ የስራ ዕድሎች መክነዋል”
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:58 0:00


XS
SM
MD
LG