በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለ አዳዲሶቹ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች- ቆይታ ከዶ/ር ኤርሚያስ በላይ ጋር


በህንድ ሙምባይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ .
በህንድ ሙምባይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ .

የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች መገኘታቸው ለዓለም አንጻራዊ እፎይታ በሰጠበት በአሁኑ ሰዓት ፣አዳዲስ የቫይረሱ ዝርያዎች በተለያዩ ሀገራት መፈጠራቸው ሌላ ስጋት ደቅነዋል። አዳዲሶቹ ቫይረሶች በእንግሊዝ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ብራዚል የተቀሰቀሱ እና ወደ ሌላው የዓለም ክፍል በመስፋፋት ላይ የሚገኙ ናቸው።

ስለ አዳዲሶቹ ዝርያዎች ምንነት እና ሊፈጥሩት ስለሚችሉት ተግዳሮት ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም ዶ/ር ኤርሚያስ በላይን አነጋግሯቸዋል። ለመርሐ-ግብራችን እንግዳ ያልሆኑት ዶ/ር ኤርሚያስ አትላንታ ጆርጂያ በሚገኘው የዮናይትድ ስቴትስ በሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከለከያ ማዕከል (CDC) ውስጥ ፣ ከተላላፊ በሽታዎች ጋር በተያያዘ ጥናት እና ምርምር የሚደርግ ፣መከላከያ መላዎችንም የሚያቀብል የስራ ክፍል ተባባሪ ሃላፊ ናቸው።

የአሁኖቹ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎችን ቀደም ብሎ ከነበረው ዝርያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አስቀድመው ያስረዳሉ።

መልካም ቆይታ !

ስለ አዳዲሶቹ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች -ቆይታ ከ ዶ/ር ኤርሚያስ በላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:11 0:00


XS
SM
MD
LG