በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትግራይ ክልልን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ እየሠራ መሆኑን መንግሥት ገለፀ


መቀሌ ከተማ
መቀሌ ከተማ

መንግሥት ትግራይ ክልልን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ እየሠራ መሆኑን አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ባዘጋጀዋው የጥያቄና መልስ ማብራሪያ ላይ ገለፀ።

ባለፈው ሣምንት ሐሙስ ጥር 20/2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ቡድን “አትላንቲክ ካውንስል” የተሰኘ የዩናይትድ ስቴትስ የሐሳብ አብላዮችተቋም ባዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ላይ ትግራይ ክልልን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያእንደሰጠ በሚኒስቴሩና በካውንስሉ ድረ ገፅ ላይ ይፋ ተደርጓል።

ለአድን ሰዓት በቆየው በዚህ የጥያቄና መልስ ውይይት ላይ ከአዲሱ ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር አባላትእና እንደራሴዎች መካከል የተገኙ እንደነበሩ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ ያሳያል። በሌላበኩል በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ፤“ወደ 30 የሚሆኑ ሰዎች እንደተሳተፉ አይቻለሁ” ብለዋል።

ማብራሪያው ለምን ተዘጋጀ?

አምባሳደር ፍፁም አረጋ መርኃግብሩን ያዘጋጀውና ተጋባዦችን የጠራው አትላንቲክ ካውንስል መሆኑን ይናገራሉ። በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ደግሞ ማብራሪያውን የሰጡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እናየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋንሁሴን እና የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጄንስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ናቸው።

በዕለቱ በስብሰባው ላይ የተገኙት በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ፤ የማብራሪያ መርኃግብሩ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ጉዳይ ለሚያሳስባቸው መረጃ ለመስጠት እንደሆነ ገለፀው፤“በኢትዮጵያ ጉዳይላይ የተለያዩ መረጃዎች እየተሠራጩ ስላሉ የኢትዮጵያ መንግሥትን ትክክለኛ ሐሳብና ስልት እንዲሁምደግሞ በየወቅቱ እየሆኑ ያሉ ነገሮችን ትክክለኛ ግንዛቤ ለመስጠት ነው” ብለዋል።

ትግራይ ክልልን በተመለከተ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የሚነሱት ጥያቄዎችእና የሚሰነዘሩት ክሶች በዛ ያሉ ናቸው። “ትግራይ ክልል ወረራ የተፈጸመበት ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትነው” ከሚለው “የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን በጋራ ሆነው ጥቃት ፈፅመዋል” የሚለውም ይጠቀሳል። “በጦርነቱ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች መሰረተልማቶች ፈራርሰዋል፣ ዘረፋ ተፈፅሟል” የሚል ክስም ይቀርባል።

ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህንን እርዳታ ለመስጠት የሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ደግሞ እንደልብ ተንቀሳቅሰው እርዳታውን መለገስ አልቻሉም። በዚህም የተነሳ በአሁኑ ሰዓትም የሰብዓዊ ቀውስ ቀውሱ እየተባባሰ ነው። የወደፊቱም በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚሉ ስጋቶችም በመንፀባረቅ ላይ ይገኛሉ።

የኤርትራ የወታደር ክፍልም ከኢትዮጵያ መከላከታ ሠራዊት ጋር ተሰልፎ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እያደረሰ እንደሆነ በስፋት ይገለፃል። ግድያ፣ዘረፋ፣መደፈር እና ሌሎች ኢ- ሰብዓዊ የሆኑ ጥቃቶች በክልሉ እንደደረሱምዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በሚያወጧቸው ሪፖርቶች እየገለፁ ይገኛሉ። አዲሱ የፕሬዚዳንት ጆባይደን አሰተዳደር በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አማካኝነት ባለፈው ሳምንት በሰጠው መግለጫም የኤርትራወታደሮች ከትግራይ ክልል በአስቸኳይ እንዲወጡ ጠይቋል።

አምባሳደር ፍጹም አረጋ በአትላንቲክ ካውንስል በነበረው የማብራሪያ ውይይት ላይ እነዚህ እና ሌሎች ጥያቄዎችም በማብራሪያው ወቅት መነሳታቸውን ጠቅሰው። በዕለቱ ለእያንዳንዱ ጥያቄዎች የተሰጡትን ምላሾች ዘርዝረዋል።

“የሕወሓት ጽንፈኛ አመራር ቡድን በሰጠው አመራር መከላከያ ሠራዊታችን ላይ ከፍተኛ የአገር ክህደትጉዳት ጭምር አድርሰዋል። ግድያና የጦር መሳሪያ ዘረፋ እንዲሁም ሌሎች ድርጊቶች በማድረጋቸውመንግሥት ለዛ አፀፋ መልሷል። እዚህ ላይ ያለውን ብዥታ ጦርነቱን ማን እንደጀመረው በራሳቸው ሚዲያ ጭምር የገለጹት በመሆኑ ሁሉም ሁኔታውን በሚገባ እየተከታተለው ነው” ብለዋል።

“እስካሁን በ92 የማሰራጫ ጣቢያዎች የእህል አቅርቦት በመንግሥት በኩልእየቀረበ ነው። እና የምግብም፣ የመድኃኒትም በአጠቃላይ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፎች እየተሰጡ ነው”

የመንግሥት ባለሥልጣናቱ ሲያስረዱ የነበረው የሰብዓዊ እርዳታውን በተመለከተ መሆኑን የገለጹትአምባሳደር ፍፁም አረጋ፤ “እስካሁን በ92 የማሰራጫ ጣቢያዎች የእህል አቅርቦት በመንግሥት በኩልእየቀረበ ነው። እና የምግብም፣ የመድኃኒትም በአጠቃላይ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፎች እየተሰጡ ነው” ካሉ በኋላ እነዚህ ቁሳቁሶች እየተሠራጩ ስላሉበት ሁኔታ በዝርዝር ቀርቧል ብለዋል።

ትግራይ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት እርዳታ የሚያስፈልገው ሰው ቁጥር 4.5 ሚሊዮን እንደሆነ የክልሉ ጊዜያዊአስተዳደር የማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃ ደስታ ዳሰሳ ጥናት ማድረጋቸውን ገልፀው ለአሜሪካ ድምፅ መናገራቸው ይታወሳል። በመንግሥትና እና በእርዳታ ሠራተኞች መካከል ከተደረገ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ መረጃ በሚል በዚህ ዙሪያ ዘገባ ያስነበበው አሶሼትድ ፕሬስም ፤ በምግብ እጥረት የተነሳ በትግራይክልል ሰዎች ሕይወታቸው ማለፍ ጀምሯል ብሏል።

ቁጥሩን የተመለከተው ጥያቄ በአትላንቲክ ካውንስሉስብሰባ ላይ ቀርቦ ነበር ያሉት አምባሳደር ፍፁም የመንግስትን ምላሽ ሲያስረዱ፤ “የሕግ ማስከበር እርምጃው ከመጀመሩ በፊት ትግራይ ውስጥ 1.8 ሚሊዮን ሕዝብ በሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ታቅፎ እርዳታእያገኘ የሚኖር ሕዝብ ነበር። ግጭት ደግሞ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውንም ሆነ ብዙ ነገሩንስለሚያስተጓጉል ወደ 700 ሺሕ የሚሆን ተጨማሪ ሕዝብ ለዚህ ችግር እንደተጋለጠ ነው። ስለዚህበድምሩ 2.5 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ተገቢው እርዳታ ያስፈልገዋል። ለአንድ ወር የሚሆን እርዳታምመንግሥት በእነዚህ የሥርጭት ጣቢያዎች እያደረሰ ነው” ብለዋል።

“የሕግ ማስከበር እርምጃው ከመጀመሩ በፊት ትግራይ ውስጥ 1.8 ሚሊዮን ሕዝብ በሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ታቅፎ እርዳታእያገኘ የሚኖር ሕዝብ ነበር። ግጭት ደግሞ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውንም ሆነ ብዙ ነገሩንስለሚያስተጓጉል ወደ 700 ሺሕ የሚሆን ተጨማሪ ሕዝብ ለዚህ ችግር እንደተጋለጠ ነው። ስለዚህበድምሩ 2.5 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ተገቢው እርዳታ ያስፈልገዋል። ለአንድ ወር የሚሆን እርዳታምመንግሥት በእነዚህ የሥርጭት ጣቢያዎች እያደረሰ ነው” 

የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ከዚህ በላይ እንደሆነ የሚናገሩ ሰዎች የሚጠቅሱት ቁጥር ግምት እንደሆነምገልፀዋል። “ብዙዎቹ ይህን እየሰጡ ያሉ እዛ ገብተን ለመዘገብ መረጃውን ለመናገር አልቻልንም ይላሉ።በሌላ በኩል ደግሞ ቁጥር ይሰጣሉ። የሚናገሩት የሚጋጭ ነው። መጀመሪያ ይህን ከፍተኛ ቁጥር የተናገሩትድርጅቶች መጀመሪያ ገብተን ለማጣራት አልቻልንም ግን ደግሞ ይህን ያህል ቁጥር ሕዝብ እርዳታያስፈልገዋል” ይላሉ ያሉት አቶ ፍፁም፤ “በእርግጥ ለሕዝቡ በማሰብ ይህንን እያሉ ከሆነ በጣም ጥሩእገዛውን ያድርጉ ሕዝቡን ይደግፉት። በኛ በኩል ግን የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረጉ ሁኔታዎችእንዳሉ እናያለን።” ብለዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ በአራት የስደተኛ መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች፤በኤርትራ ወታደሮች ተይዘው ወደ ኤርትራ እየተመለሱ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ቃል አቀባይ መረጃ እንዳለው በመግለፅ በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል። አምባሳደር ፍፁም ስደተኞቹስለሚገኙበት ሁኔታም የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በካውንስሉ ስብሰባ ላይ ማብራሪያሰጥተዋል ብለዋል።

“በአጠቃላይ እንግዲህ ኢትዮጵያ አፋር ውስጥ ሁለት ፣ ትግራይ ውስጥ ደግሞ አራት በአጠቃላይ ስድስትየስደተኛ ጣቢያዎች እንዳሉ ይታወቃል። ከአራቱ ውስጥ ሁለቱ ወደ ድንበር ሁለቱ ደግሞ ወደ መሃል ሽሬእንደነበሩ ይታወቃል። እነሱም ያሉበት ሁኔታ በሕግ ማስከበር ውስጥ የነበረ ችግር እንደነበረ አሁን ግንበተለይ መካከል አካባቢ ያሉት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የተባበሩት መንግሥታት ደርሶ ተገቢ ድጋፍእስኪሰጣቸው ድረስ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በብድር መልክ የሚያዝ የተለያዩ የምግብ አቅርቦቶችእየተደረገ እንደሆነ እነዚህ ሁሉ ለጉብኝት ክፍት መሆናቸው ተገልፆላቸዋል” ሲሉ ሰፋ ያለ ማብራሪያሰጥተዋል።

የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ክልል መኖራቸው ብቻ ሳይሆን ኖረውም የሰብዓዊመብት ጥሰት እየፈፀሙ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲወጡ የዩናይትድ ስቴትስ የጆ ባይደን አስተዳደር በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ በኩል ባለፈው ሳምንት ጠይቋል። ሌሎች ተመሳሳይ ሪፖርቶችምእየተሰሙ ይገኛሉ። አምባሳደር ፍፁም አረጋ ይህ ጥያቄ በአትላንቲክ ካውንስሉ ስብሰባ ላይ አልቀረበምወይ ከቀረበስ የኢትዮጵያ መንግስት ምን ምላሽ ሰጠ? ምላሹስ ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ አምባሳደርፍፁም ሲመልሱ፤

“የኤርትራ ወታደሮች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ በሚል በተደጋጋሚ የሚገለፅ ነገር አለ። ይሄን በተመለከተየኤርትራ መንግሥት አልገባሁም ብሎ መግለጫ ሰጥቷል። ሁለተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራወታደሮችን ግብዣ እንዳላቀረበ መኖራቸውንም እንዳላረጋገጠ ነው በተደጋጋሚ እየተነገረ ያለው።” ካሉበኋላ አያይዘው ሲመልሱ፤ “አንድ ግልፅ መሆን ያለበት ነገር ምንድነው? ድንበሩን የሚጠብቁ ወታደሮችጥቃት ሲደርስባቸው ድንበሩን የሚጠብቅ ማንም የለም። የኢትዮጵያ ሠራዊት በሕወሓት ጽንፈኛ ቡድንየተያዘውን ቦታ እያስለቀቀ ድንበሩ ድረስ እስኪደርስ ድረስ የኤርትራ ወታደሮች ገብተዋል አልገቡምየሚለውን የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያረጋግጥበት የሚችልበት መንገድ ያለ አይመስለኝም። በዛ መካከልየተፈጠረውን ክፍተት የኤርትራ መንግሥት የሰጠውን መግለጫ ከመውሰድ ባለፈ የተለየ ነገር ማለትአስቸጋሪ ነው የሚሆነው።” ብለዋል።

በየቦታው የደረሱ በደሎችና ዘረፋዎች ስለመኖራቸው በአትላንቲክ ካውንስሉም ላይ መቅረቡንያስታወሱት አቶ ፍፁም፤ “ የሕወሓት ጽንፈኛ ቡድን እየለቀቀ በሄደበት ግዜ ወደ 13 ሺሕ የሚደርሱበከፍተኛ ወንጀል የታሠሩ ሰዎችን ለቆ ስለነበር እነዚህ የተለቀቁ አካላት አንዳንድ ቦታ ታጥቀውምጭምር ከፍተኛ በደል ሊያደርሱ እንደሚችሉ ጥቆማ እየመጣ እንደሆነ ባለሥልጣናቱ ማብራሪያሰጥተዋል” ብለዋል።

በሌላ በኩል እሁድ ዕለት ይህንን ውይት መነሻ አድርጎ ዘገባ ያጠናቀረው አሶሼትድ የኢትዮጵያ መንግስትበክልሉ ነገሮች ወደነበሩበት እየተመለሱ ነው በሚል የብሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደርስ ሰዎች ባሉበትቢናገርም የዓይን እማኞች ግን ትግራይ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የረሃብ ስጋት እንዳለ ይገልፃሉ።

በትግራይ ክልል ውስጥ ከተከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ ጎን ለጎን ተያይዞ የሚነሳው አሁንም ውጊያ መኖሩሲሆን ይህንን በተመለከተ ሰሞኑን ለዓለም የሰላም ፋውንዴሽን ከትግራይ ገጠራማ ቦታ ሆነው በስልክቃለ ምልልስ እንደሰጡ የተገለፀውን የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ሙሉጌታገብረሕይወትን ቃል ጠቅሶ ኤፒ እንደዘገብው፤ በትግራይ ክልል አሁንም ውጊያው መቀጠሉን የኤርትራወታደሮች የአርሶ አደሩን ሰብል ካቃጠሉና ከዘረፉ በኋላ በኤርትራ ድንበር አካባቢ የሚገኙ ገበሬዎችበረሃብ መካከል መሆናቸውን ገልፀዋል።

በቅርቡም ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ሊከተል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን አጋርተዋል። በሌላ በኩል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ለጋሾች ሙሉ ለሙሉ ትግራይ ክልልእንዲገቡ በሚጠይቀው ማሳሰቢያው አሁንም በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ውጊያው እንደቀጠገልጿል።

በሌላ በኩል በክልሉ ያለውን የጤና ሽፋን ሁኔታ በተመለከተ የድንበር የለሽ ሃኪሞች ማኅበር የትግራይክልል የአስቸኳይ ግዜ አስተባባሪ አልበርት ቪናስ ከታኅሣሥ ወር ጀመሮ ወደ ትግራይ ክልል ተጉዘውአዲግራት፣ አክሱም እና ዐድዋን ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ፤ ከሁለት ቀናት በፊት በድርጅቱ ድረ ገፅ ላይባስነበቡት አዲስ ሪፖርት፤ በትግራይ ክልል ገጠራማ አካባቢዎች ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ማወቅባለመቻሉ ስጋት እንዳላቸው ነገር ግን ከአካባቢው ሽማግሌዎች መረዳት እንደቻሉት ሁኔታዎች እጅግአስቸጋሪ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በአዲግራት ከተማ ከፍተኛ ውጥረት መኖሩን፣በሆስፒታሎች ውስጥ ያለው ሁኔታም እጅግ አስቸጋሪእንደሆነ፣ ምግብ፣ ውሃ እና ገንዘብ እንደሌለ መመልከታቸውን በሪፖርታቸው አስነብበዋል። በሆስፒታልውስጥ የተኙት አንዳንዶቹ ታካሚዎች አሰቃቂ ጉዳቶች እንደደረሱባቸው አንዳንዶቹ ደግሞ በምግብእጥረት እንደተጎዱ መመልከታቸውን አስረድተዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 2.3 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በትግራይክልል የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቅሶ፤ በግራይ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ መፈፀሙን፣የቦንብ ድብደባ መድረሱን፣ ግድያ እና ዘረፋ እንዲሁም በሴት ልጆች ላይ ጾታዊ ጥቃት መፈፀሙ  ጠቅሶበአሁኑ ሰዓት 450 ሺሕ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል ብሏል። እነዚህን ዜጎች ለማገዝምመንግሥት ሙሉ ለሙሉ በሩን ለረድኤት ድርጅቶች መክፈት አለበት ሲል አሳስቧል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 2.3 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በትግራይክልል የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቅሶ፤ በግራይ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ መፈፀሙን፣የቦንብ ድብደባ መድረሱን፣ ግድያ እና ዘረፋ እንዲሁም በሴት ልጆች ላይ ጾታዊ ጥቃት መፈፀሙ ጠቅሶበአሁኑ ሰዓት 450 ሺሕ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል ብሏል። እነዚህን ዜጎች ለማገዝምመንግሥት ሙሉ ለሙሉ በሩን ለረድኤት ድርጅቶች መክፈት አለበት ሲል አሳስቧል።

በተያያዘም ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ኮሚሽነርፊሊፖ ግራንዲ ከጉብኝታቸው በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የተባበሩት መንግሥታት ተቋማትናመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በክልሉ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ እጅግ መሰረታዊ መሆኑን ገልፀው 25 መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ወደ ትግራይ ክልል እንዲገቡ ፍቃድ እንዲሰጣቸው በመጠባበቅ ላይመሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚሁ መግለጫቸው ላይ ትግራይ ክልልን በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያ ብዙ የተለያዩ ነገሮችእንደሚነገሩም ገልፀው ፤ እንደርሳቸው ቦታውን በአካል ተገኝቶ ለተመለከተ ግን ሁኔታው ምን ያህልየተወሳሰበ መሆኑን መገንዘብ እንደሚቻል ጥቆማ ሰጥተዋል። በርካታ የተኩስ ልውውጦች እና ጥሰቶችበሁሉም ወገኖች እንደነበሩና በገለልተኛ አካላት ምርመራ ሊደረግ እንደሚገባም ገልፀዋል። ሁኔታዎችተባብሰው ከቁጥጥር ውጭ ሳይወጡ አስቸኳይ እርዳታ በመስጠት ሰብዓዊ ቀውሱን ማስቆምእንደሚገባም ጠቁመዋል።

(የዘገባውን ሙሉ ክፍል ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ላይ ማዳመጥ ትችላላችሁ)

ትግራይ ክልልን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ እየሠራ መሆኑን መንግሥት ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:07 0:00

(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

XS
SM
MD
LG