በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማህበራዊ ሚዲያ ለብሩህ ህልሞች፦ቆይታ ከሚሪያም ዓለሙ ጋር


የመንፈስ ንቃት እና የግል ዕድገት አሰልጣኝ ሚሪያም ዓለሙ..
የመንፈስ ንቃት እና የግል ዕድገት አሰልጣኝ ሚሪያም ዓለሙ..

ኢትዮጵያዊያን የሚያዘወትሯቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች ቤተኛ የሆነ ሰው ሚሪያም ዓለሙ እንግዳ አትሆንበትም። በዕየለቱ በምታቀርባቸው በቪዲዮ የታገዙ አነቃቂ ንግግሮች እና የህይወት ምክሮች በርካቶች ያውቋታል።

የግላዊ ዕድገት አሰልጣኝ እና አማካሪም የሆነችው ሚርያም ከአራት ዓመታት በላይ በዘለቀ አገልግሎቷ ብዙሃን የሚገጥሟቸውን ችግሮች አንስታ መፍትሄ የምትላቸውን አጋርታለች።ለተጨማሪ ንግግር እና ውይይት መነሻ የሚሆኑ ጉዳዮችን በመምዘዝ የማህበራዊ መገናኛ አዘውታሪዎች ብሩህ አለሚዎች እንዲሆኑ ስታበረታታም ሰንብታለች።

ሚሪያም ሰዎች መንፈሳቸውን የሚያነቃቁባቸውን መንገዶች ከመምከር ባሻገር ግን ጠንካራ ስራ እንደሚጠብቃቸው ለመጠቆም “ማነቃቂያ ብቻውን ዋጋ የለውም፤ ትምህርትም ብቻውን ዋጋ የለውም። ዋጋ የሚኖረው እኛ እርምጃ ስንወስድ ነው!” ስትል ታስገነዝባለች።

ስለወጣቷ የበይነ መረብ ላይ አገልግሎት የበለጠ ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም ከሚሪያም ጋር በስልክ አጭር ቆይታ አድርጓል። ሙሉ ቆይታውን ያዳምጡ።

ማህበራዊ ሚዲያ ለብሩህ ህልሞች፦ቆይታ ከግል ዕድገት አሰልጣኝ ሚሪያም ዓለሙ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:26 0:00


XS
SM
MD
LG