የተሰናባቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች
ዕረቡ ታኅሣሥ 28/2013 ዓ.ም የሃገሪቱ ምክር ቤት የሚገኝበት ሕንፃ በመውረር እና ወደ ውስጥ በመግባት የፈፀሙት ድርጊት በዓለም ዙሪያ ድንጋጤን ፈጥሯል። ሐዘናቸውን የገለፁና ምፀትየቀላቀለበት ምላሽ የሰጡም በርካቶች ናቸው።
በኢሌክቶራል ኮሌጅ ድምፅ (ባለ ድምፅ ተወካይ መራጮች ድምፅ) የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው የተነገረው ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ውጤትን ማረጋገጫ ለመስጠት የምክር ቤት አባላቱ በተሰበሰቡበት የተከሰተው ረብሻናየታየው ወረራ በምክር ቤቱ የሪፐብሊካንም ሆነ የዴሞክራት አባላት ውግዘት ደርሶበታል።
በሌላ በኩል የትራምፕ ደጋፊዎች ድርጊቱን የፈጸሙት ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ኅዳር ወር በተካሄደው ምርጫ አሸንፈው ሳለ ተሸንፈዋል በመባሉ የተሰማቸውን ቁጣ ለመግለጽ መሆኑን ሲናገሩ ተሰምተዋል። ነገር ግን ድርጊቱ ዴሞክራሲን ፍጹም የተፃረረ ነው በሚልየገጠመው ተቃውሞ አይሏል።
በዚህ ድርጊት የተሰማቸውን በቪዲዮ በተቀረፀ መልዕክት በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት የፈረንሳዩ ፕረዚዳንት ኢማኑየል ማክሮን፣ “ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈጸመው ተግባር፣ የአሜሪካን ባሕሪ አያንጸባርቅም ብለዋል። “በዲሞክራስያችንና በአሜሪካ ዲሞክራሲእንተማመናለን” ሲሉም አክለዋል።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናረንድራ ሞዲ፣ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ “በዋሽንግተን ያየሁት መነሳሳትና ግጭት አሳዝኖኛል፣ ዲሞክራስያዊው ሂደት በህገ-ወጥ ተቃውሞ እንዲሰናከል መፈቀድ የለበትም” ብለዋል።
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በግጭቱ የተሰማውን ሐዘን ገልጿል። በዋሽንግተን ዲሲ የተደነገገውን የሰአት ኃላፊ ገደብን መሰረት በማድረግ፣ ዋሽንግተን ውስት የሚኖሩ የታይዋን ዜጎች፣ ጥንቃቄ እዲያደርጉ መመከሩን ጠቁሟል።
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ ዛይድ ሃፌዝ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የሃገራቸው መንግሥት፣ ዋሽንግተን ያለውን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ መሆኑን ገልፀዋል። ብሁኔታዎች በፍጥነት ተረጋግተው፣ መነሳሳቱ በስልጣን ሽግግሩ ሂደት ላይ፣ተጽዕኖ እንደማይኖረው ተስፍ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል።
የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ኻን ልዩ ረዳት ራኦፍ ሃሰን ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል፣ የተወካዮች ምክር ቤትና የመወሰኛ ምክር ቤት አባላት፣ ተመራጩ ፕረዚዳንት ማሸነፋቸውን፣ በመራጮች ተወካዮች መረጋገጡን በሚመሰክሩብት ጊዜ፣ የትራምፕ ጽንፈኛ ደጋፊዎች ወደ ምክር ቤቱ ሕንጻ ገፍተው ሲገቡ ሲታይ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሌሎች ሃገሮች፣ የዲሞክራ መርህ አተገባበር ላይ የመተቸት፣ የሞራል ልዕልና እንደሌላት ያሳያል ብለዋል።
በማሌዢያ የስትራተጂና ዓለም አቀፍ ጥናቶች ተቋም የሚሰሩ ተንታኝ ሻርመን ሎክማን በበኩላቸው፣ “የመነሳሳቱ ተግባር የአሜሪካን ገጽታ አያስምርም ሲሉ”፣ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። ሰዎች በአሜሪካ ላይ ያላቸውን አሉታዊ አመለካከት ያጎላብታል ብለዋል።
በፖለቲካ እድገቷ እና በመንግስት ስርዓቷ ዩናይትድ ስቴትስን እንደ ተምሳሌት የምቆጥረው ድቡብ ኮሪያ በአሜሪካ ምርጫውን ተከትሎ በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ እየታኬደ ባለው ብጥብጥ ግራ መጋባቷን እያሳየች ነው።
ቀደም ሲል በጠንካራ ወታደራዊ አገዛዝ ስር የነበረችውና በአሁኑ ወቅት በእስያ ጠንካራ ዲሞክራሲ በመገንባት የምትታወቀው ደቡብ ኮሪያ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በነዚህ ድርጊቶች ግራ የተጋቡ ሲሆን በዋሽንግተን እየታየ ያለውን ሻካራ የስልጣን ሽግግርመፀየፋቸውንም እየገለፁ ነው።
የደቡብ ኮሪያ መንግስት በአሜሪካ ምክር ቤት ህንፃ ላይ በደረሰው በጉልበት ሰብሮ የመግባት ተግባር ላይ እስካሁን አስተያየቱን ባይሰጥም የሀገሪቱ ዋና ሕግ አውጪ የሆኑት ሶንግ ዮንግ ጂል በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ ይህ የዩናይትድ ስቴትስን አሳፋሪ ገፅታ ያሳየ ነው ሲሉ አስፍረዋል።