ዋሽንግተን ዲሲ —
በዩናይትድ ስቴትስ ባሳለፍነው ሳምንት 787 ሺሕ ሠራተኞች የሥራ አጥነት ክፍያ እንዲከፈላቸው ማመልከታቸውን የሀገሪቱ ሠራተኞች መስሪያቤት አስታወቀ። መስሪያ ቤቱ ይህን ያለው መንግሥት ብዙዎችን ያላስደሰተውን ለሥራ አጦች በየሳምንቱ የሚሰጠውንየ300 ዶላር ድጎማ መስጠት በጀመረበት ወቅት ነው።
ላለፉት ዐሥር ወራት የኮሮና ቫይረሰ ወረርሽኝ የአሜሪካ ሠራተኞች ላይ የፈጠረው ጫን በቀጠለበት ወቅት በየሳምንቱ 3 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች የድጎማ ጥይቄ የሚያቀርቡ ሲሆን ከታኅሣሥ ወር መጨረሻ ጀምሮይህ ቁጥር ለውጥ አላሳየም።
በአሜሪካ ከሚገኙ 22 ሚሊዮን ሠራተኞች መካከል ሥራቸውን ያጡ 10 ሚሊዮን ሰዎች እስካሁን ሥራ አላገኙም። የሥራ አጥነት ቁጥሩ በኅዳር ወር ላይ 6.7 ከመቶ የነበረ ሲሆን በመጪዎቹ ወራቶች በዚሁ መልኩ እንደሚቀጥልም የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የሠራተኞች ቅጥር ለአምስት ተከታታይ ወራት እየቀነሰ የሄደ ሲሆን ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የወጡ አዳዲስ ቅጥሮች በጣም ዝቅተኛ መሆናቸው ታውቋል።