በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምክር ቤቱ ሕንፃ ጠባቂዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ተጠይቋል


የ2020 የአሜሪካው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ማን እንደሆነ ማረጋገጫ ለመስጠት የምክር ቤቱ አባላት በተሰበሰቡበት በትላንትናው ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ የተሰናባቹ ትራምፕ ደጋፊዎች ከሕግ አሰከባሪዎች ጋር ግብግብ ገጥመው
የ2020 የአሜሪካው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ማን እንደሆነ ማረጋገጫ ለመስጠት የምክር ቤቱ አባላት በተሰበሰቡበት በትላንትናው ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ የተሰናባቹ ትራምፕ ደጋፊዎች ከሕግ አሰከባሪዎች ጋር ግብግብ ገጥመው

በትላንትናው ዕለት የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ አውጭዎች ምክር ቤት ሕንጻን በመውረር፣ የተፈጸመውን ድርጊት አስመልከቶ በምክር ቤቱ ሕንጻ ጠባቂ ፖሊሶችና ሕግ አሰከባሪዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ የምክር ቤት አባላት ጠይቀዋል፡፡

ሕግ አውጭዎቹ የምክር ቤት አባላት የትናንቱን ሁከት በመቆጣጠር ከፍተኛ ተጋድሎ ይደረጉትን የፖሊስና ሕግ አስከባሪ አካላት አድናቆታቸውን ቢገልጹም ቀድሞውኑም ቢሆን እንዲህ ያለ ነገር እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

በተለይም በአዲሱ ሕግ አውጭ ምክር ቤት የምክር ቤቱን ሕንጻና አስተዳደር በጀት ኮሚቴ የሚመሩት ሁለቱ ዴሞክራቶች ፣ ድርጊቱን በዝርዝር የሚያመላክቱ ብዙ ቪዲዮች እንዳሉ በመግለጽ “አንዳንዶቹ ጀግንነትን የሚያሳዩ ቢሆንም አንዳንዶቹ ግን አሳሳቢ ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡ ስለዚህ ሙሉ ምርመራ ተደርጎ የምክር ቤቱ ህንፃ በዚያ ፍጥነት እንዴት ሆኖ ሊወረር እንደቻለ የጥበቃውና የደህንነቱ ሁኔታ እንደገና ሊመረመር ይገባዋል ብለዋል፡፡

“የፕሬዘዳንትን መሰረት ቢስ ቅሰቀሳ ሰምተው ቀደም ሲል ለተቃውሞ አመጽ የተዘጋጁ ሰዎች መኖራቸው እየታወቀ ለምን በቂ ዝግጅት አልተደረገም?” የሚሉ ጥያቄዎችም የምክር ቤት አባላቱ አንስተዋል፡፡

የምክር ቤት አባል የሆኑት ኢልሃን ኦማር “ለብሄራዊ ደህንነት ጥበቃ በቢሊዮን ዶላሮች እናወጣለን፡፡ በዛሬው እለት በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ህገ ወጥ ነውጠኞች ያደጉትን ወረራ ግን ማስቆም አልቻልንም፡፡ ይህ ተቀባይነት የለውም!” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴት ምክር ቤት በዓመት ወደ 460 ሚሊዮን በጀት የሚመደብለት ሲሆን ከ2ሺ 300 በላይ ሲቪል ሠራተኞችም እንዳሉት ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG