በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ኢቲ ስማርት አር ኤስ ኤስ ( ET-Smart-RSS) የተባለች ሳተላይት አምጥቃለች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በቻይና ድጋፍ ወደ ጠፈር የተላከችው የዚህች ሁለተኛ ሳተላይት ሥራ የመሬት ምልከታ መረጃ ማሰባሰብና ወደ ምድር ጣቢያ መላክ መሆኑን የኢትዮጵያ የጠፈር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትአስታውቋል።

ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ETRSS-1 የተባለች የመጀመሪያዋን ሳተላይት ባለፈው ዓመት ታኅሣስ 2012 ዓ.ም ማምጠቋ ይታወሳል።

“ETRSS-1” መሬትን እየቃኘችና በፎቶ የተደገፉ መረጃዎችን እየላከች መሆኗን የጠፈር ሳይንስ እናቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ይሽሩን ዓለሙ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ሳተላይቷ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶችን ለማግዝ፣ ከግብርና ጋር የተያያዙጥናትና ምርምሮችን ለማከናወንና ሌሎች ለመሠረተ ልማት አገልግሎት የሚውሉ መረጃዎችንበማሰባሰብ ላይ ስትሆ ትናንት የመጠቀችው ET-Smart-RSSም ከቀድሞዋ ETRSS1 ጋር ተመሳሳይ ተልዕኮእንዳላት ዶ/ር ይሽሩን ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ኢትዮጵያ ኢቲ ስማርት አር ኤስ ኤስ ( ET-Smart-RSS) የተባለች ሳተላይት አምጥቃለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:30 0:00


XS
SM
MD
LG