በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት ለስደተኞችና ተፈናቃዮች የ455 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ተማጽኗል


የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ፣ ስደተኞችንና ተፈናቃዮችን፣ከአስከፊው የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ455 ሚሊዮን ዶላር እርዳታተማጽኗል፡፡

ሁሉም ሰው ለኮረና ቫይረስ ተጋላጭ ቢሆንም ስደተኞች፣ ተፈናቃዮችና፣ አገር አልባ ሰዎች ደግሞበከፍተኛ ደረጃ በቫይረሱ ለመያዝና ለሞት የበለጠ ተጋላጮች ናቸው፡፡ በመንግሥታቱ ድርጅት፣ወረርሽኙ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ፣ በ13 አገሮች ላይ በተደረገ ክትትል፣ 74 ከመቶ የሚሆኑ ስደተኞችከመሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው ግማሹን እንኳ ማሟላት የቻሉ አይደሉም፡፡ ይህ ሁኔታቸው ወረርሽኙከመከሰቱ በፊት ከነበረው 2019 ዓም በ21 ከመቶ ጨምሯል፡፡

ይህ በመሆኑም፣ ከ80 ከመቶ በላይ የሚሆኑት፣ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ፣ ንብረታችን ለመሸጥ፣የወሲብ አገልጋይ በመሆንና በህጻንነት ጉልበታቸው ወደ ሥራ በመሥራትና ለመበዝበዝ ተገደዋል።የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ ቃል አቀባይ፣ ባባር ባሎች እንደሚሉት፣ ከተማውስጥ ያሉ ስደተኞች፣ መሠረታዊ ፍጆታቸውን ለማሟላት የሚተማመኑት፣ የቀን ሥራ ሠርተውበሚያገኙት ገቢ ነው።ይሁን እንጂ፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ፣ ሁሉም ነገር የተዘጋጋ በመሆኑ፣ኑሯቸውና ሥራቸውም ተጎድቷል።

በወረርሽኙ የተነሳ፣ በተጣለው ገደብ፣ ብዙ ቦታዎችና መገበያያዎች በመዘጋታቸው ሁሉም ከአካባቢውጠፍተዋል፡፡ ስለዚህ፣ ተስፋ የቆረጡ ስደተኞች መሠረታዊ ፍጆታዎቻቸውን ለማሟላትና፣ ለኑሯቸውአስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶቹን ለመጠቀም እንኳ እንዲችሉ በእጃቸው ጥሬ ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ባሎች እንደሚሉት፣ ስደተኞቹ አክባቢያቸው የተጨናንቀ በመሆኑ፣ የአካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅአልቻሉም፡፡ እንደ ውሃ፣ ሳሙና፣ እና ጤንነታቸውን የተጠበቀ ለማድረግ የሚረዱ ነገሮችን ሟሟላትምእጅግ አስፈላጊ ነገር መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በዚሁ ሁኔታ ውስጥ፣ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንምአንስተዋል።

“በሱዳን ያለው ገጽታ ብትመለከቱ፣ ከኢትዮጵያ በቅርቡ ወደ ሱዳን የመጡ ስደተኞች አሉ፡፡ ያ ትልቅፈተና ነው፡ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በቦታው የደረሱ ከ51ሺ በላይ ስደተኞች በድንበር አካባቢዎችተሰራጭተዋል፡፡ ስለዚህ እነሱም ሆኑ የሚያስተናግዳቸው ማኅበረሰብም ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተጠበቁመሆናቸውን ማረጋገጥ ከባድ ፈተና ነው፡፡” ብለዋል።

የመንግሥታቱ ድጅርጅት እንደሚለው፣ በእጅ ያለው የገንዘብ እርዳታ እጅግ አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎችውስጥ ላሉ ስደተኖች እየዋለ ነው፡፡ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ አስፈላጊ ነገሮች ላይ በማተኮር እንኳ የብዙሰዎችንም ህይወት ማሻሻል እንደሚቻል ያምናል፡፡ ከዚያም አልፎ፣ የሚገኘው ገንዘብ፣ የጾታ ጥቃቶችንለመከላከል፣ ሰዎችን ከብዝበዛ ለመታደግ፣ የአእምሮ ጤንነትና የስነልቦና ምክር አገልግሎቶችንለመስጠት እንደሚውል ዘርዝሯል፡፡

ትምህርትንም ቀዳሚ በማድረግ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ ትምህርት ቤቶች፣ እንደገና የሚከፈቱበትንመንገድም ለማመቻቸት እንደሚሠራ፣ ያን ማድረግ አስቸጋሪ በሆነበት ሁኔታ ውስጥም፣ ኢንተርኔትንበመጠቀም በርቀት ትምህርት ኢንቨስት እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ለስደተኞችና ተፈናቃዮች የ455 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ተማጽኗል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:58 0:00


XS
SM
MD
LG