በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዳግም ግጭት በተጎራባች ወረዳዎች


በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንና በአፋር ክልል ተጎራባች ወረዳዎች በተከሰተ ግጭትበሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ግጭቱ ከዚህ በፊት ከነበረው የተለየ ገጽታ አለው ተብሏል፡፡

ከአፋር ክልል የሚጎራበተውና ግጭቱ የተከሰተበት የባቲ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ መሐመድ አብዱ ከግጦሽሳርና ከውሃ ጋር በተያያዘ ግጭቶች በተለያዩ ጊዜያት ሲከሰቱ መቆየታቸውን አስታውሰው የሰሞኑ ግጭትግን ከሌላ ጊዜው የተለየ ነው ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አህመድ የግጭቱ መንስኤ አለመታወቁን ያስረዳሉ፡፡ከአፋር ክልል በኩል ያለውን ምላሽ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ አድርገን ባይሳካልንም በክልሉ የሚንቀሳቀሱት የአፋር ዴሞክራሲዊ ፍትሃዊ ፓርቲ ሊቀመንበር መሐመድ ዳውድ፤ ሁኔታው እነርሱንም ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ዳግም ግጭት በተጎራባች ወረዳዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:38 0:00


XS
SM
MD
LG