በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል ተፈናቃዮችን ለመርዳት የ160 ሚሊዮን ተማፅኖ ቀርቧል


በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች
በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

ከሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በግጭቱ ሳቢያ ከቀያቸው ለሸሹ ስደተኞች የሚያስፈልገውን አጣዳፊርዳታ ለማቅረብ የ.ተ.መ.ድ የስድተኞች ኮሚሽነር እና 30 የሰብዓዊ ረድዔት አጋሮቹ የ160 ሚሊዮን ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ተማጽነዋል።

ገንዘቡ ለስደተኞቹ እስከመጪው የአውሮፓውያን 2021 ዓመተ ምህረት አጋማሽ የሚዘልቅ ርዳታ ለማቅረብየሚውል መሆኑን ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር አመልክቷል

“የተጠየቀው አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ቀያቸውን እየለቀቁ ወደሌላ ሃገር የሚሰደዱ ሰዎች እንቅስቃሴከቀጠለ መደረግ ያለበትን ዝግጅት ለማጠናከርም ይውላል” ብሏል።

ባለፉት ስድስት ሳምንታት ድንበር አቋርጠው ሱዳን የገቡት ኢትዮጵያውያን ከ56 ሺሕ በላይ መሆናቸውንያመለከተው ድርጅቱ፤ በቅርብ ቀናት የሚገቡት ቁጥር ቀንሶ በቀን 500 የሚጠጉ ሰዎች ይገባሉ ብሏል።“በዚህ ደረጃ የገዘፈ የስደተኛ እንቅስቃሴ ባልታየበት እጅግ የራቀ አካባቢ ለረድዒት ድርጅቶች ሥራ እጅግፈታኝ ሆኗል” ሲል የተ. መ.ድ የስደተኞች ኮሚሽነር አስረድቷል።

XS
SM
MD
LG