በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ እና በሱዳን የፀጥታ ሃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት


ማክሰኛ ዕለት በኢትዮጵያ እና በሱዳን የፀጥታ ሃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በሁለቱ አገራትከፍተኛ ባለስልጣናት ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል::

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት የግጭቱ ምክንያትድንበር ተሻግረው የገቡ የሱዳን ወታደሮች ናቸው::

የትግራዩን ሕግ የማስከበር ዘመቻ ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዩች መጠመዳችንን እንደ ጥሩ አጋጣሚመጠቀም የፈለጉ ያሏቸውን የሱዳን የበታች ባለስልጣናትም ተጠያቂ አድርገዋል::

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ቀዱም ሲል ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ወታደሮችናሚሊሽያዎች ወደ ግዛትችን በመግባት ከቅኝት ሲመለሱ በነበሩ የፀጥታ ሃይሎቻችን ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ብለዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ “ጦርነት በተቀሰቀሰበት የትግራይ ክልል አቅራቢያ በሚገኘው አጎራባቹ የኢትዮጵያድንበር አካባቢ ባለው የሱዳን የእርሻ መሬት ላይ ሱዳን ሠራዊቷን ማሠማራቷን ቀጥላለች” ሲሉ አንዳንድየሱዳን ባለሥልጣናት ባለፈው ሣምንት ተናግረው ነበር።

መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ከአካባቢ ሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለውመሆኑን ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡

"ሁለቱ ሀገራት እንዲህ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሁሌም የውይይትን አማራጭ የሚከተሉ በመሆናቸውክስተቱ የሁለቱን ሀገራት ጥብቅ ትስስር አያላላውም" ብለዋል ጠቅላይ ሚስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይባሰፈሩት አስተያየት፡፡

"ክስተቱን እንደ መልካም አጋጣሚ ወስደው በማራገብ ልዩነትን ለማስፋት የሚጥሩ አካላት የሁለቱንሀገራት ታሪካዊ ትስስር ያልተረዱ ናቸው" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በኢትዮጵያ እና በሱዳን የፀጥታ ሃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:32 0:00


XS
SM
MD
LG