በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድሬደዋ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች እያጋጠማቸው ያለውን ችግር ገለፁ


በድሬዳዋ የሚገኙ የትግራይ ክልል ተወላጆች ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጋር ተወያዩ።በውይይታቸው በድሬዳዋ ያጋጠሟቸውን ችግሮችና በትግራይ ክልል ዙሪያ ያሏቸውን ጥያቄዎች አንስተው ውይይት ተካሂዷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ባዘጋጀውና የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በተሳተፉበት የውይይት መድረክ ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን በመወከል የትምህርት ሚኒስትር ደኤታ እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ሁሪያ አሊ እና የአዲስ አበባ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊና የትግራይ ጊዜያዊ አሰዳደር ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ
ሙሉቀን ሃብቱ የውይይት መነሻ አቅርበዋል።

በመነሻውም የሕግ ማስከበር እርምጃ እንዲወሰድ መንስዔ የሆኑ ጉዳዮችንና ከቀናት በፊት በትግራይ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች በአካል የተመለከቷቸውን ጉዳዮች ጭምር አቅርበው ውይይት ተካሂዷል። የድሬዳዋ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆችም ያላቸውን ጥያቄዎችና እያጋጠሟቸው ያሉትን ችግሮች አንስተዋል። አንዳንድ ተሰብሳቢዎች በድሬዳዋ ኑሯቸው ያጋጠሟቸውን ችግሮች አንስተዋል።

(ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ)

በድሬደዋ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች እያጋጠማቸው ያለውን ችግር ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:04 0:00


XS
SM
MD
LG