በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስት አቶ ደመቀ መኮንን ፤ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ተኳቸው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባላቸው ሥልጣን ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጽ/ቤት፤ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጾ የወጣው የሹመት መረጃ መሠረት፤ የጦር ኃይሎችጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሐመድ ተነስተው በእርሳቸው ምትክ ምክትልየነበሩት ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነዋል።

በቅርቡ ጥሪ ተደርጎላቸው መከላከያውን የተቀላቀሉት ሌፍተናት ጄኔራል አበባው ታደሰደግሞ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሾመዋል።

በተጨማሪም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው ተነስተው በምትካቸው፤ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ የነበሩት ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤልንየፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

XS
SM
MD
LG