በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አማራ ክልል አዲስ ርእሰ መስተዳድር ተሾመለት


አቶ አገኘሁ ተሻገር
አቶ አገኘሁ ተሻገር

በምክትል ርእሰ መስተዳድር የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አገኘሁ ተሻገር የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሆነው በምክር ቤቱ ተሾመዋል። 

የክልሉ ምክር ቤት ይህን ሹመት ያፀደቀው ክልሉን ቀደም ሲል ይመሩት የነበሩት አቶተመስገን ጥሩነህ አሁን ባለው የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ለሌላ የሥራ ኃላፊነትመፈለጋቸውን ተከትሎ ጥያቄ በማቅረባቸው መሆኑን በመጥቀስ የሀገር ውስጥ መገናኛብዙኃን ዘገባ አስነብበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ይፋ ባደረገው መረጃም ከአማራክልል ርእሰ መስተዳድርነት የተነሱት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ የብሔራዊ መረጃና ደህንነትአገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ የነበሩት ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤልንደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

XS
SM
MD
LG