ዋሽንግተን ዲሲ —
ባለሥልጣኑ ጥገኝነት ለመጠየቅ ሱዳን የሚገኙ ስደተኞችን በተለመለከት ሀገሪቱ ምን እንደምታደርግ ገና የሚወሰን መኾኑንም ገልፀዋል። ሱዳን ይህን እርምጃ የወሰደችው በሰሜን ኢትዮጵያ፣ የትግራይ እና የፌደራሉ መንግሥት ጦርነት መግባታቸውን ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ አየር ሀይል በትግራይ የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማትን አርብ ዕለት በቦምብ መምታቱም ተዘግቧል።
ያሳለፍነው ዕረብ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ የትግራይ መንግሥት በመቀሌ ከተማ የሚገኝ የፌደራል መከላከያ ላይ ጥቃት ከፍቷል በሚል ወታደሮች ወደ ስፍራው እንዲንቀሳቀሱ ማዘዙ ይታወሳል።