ዋሽንግተን ዲሲ —
የኮቪድ 19 ሞት ቁጥርም እያሻቀበ ባለበት ሁኔታ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ለቫይረሱ የሚጋለጠው ሰው ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን አጠቃላዩ የኮሮናቫይረስ ተያዥ ቁጥር ወደ አሥር ሚሊየን እየተጠጋ መሆኑን የጃንስ ሃፕኪንስ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል ጠቁሟል።
በተለይ በመካከለኛ ምዕራብና ደቡባዊ ግዛቶች ውስጥ ኮቪድ በእጅጉ በመስፋፋቱ ምክንያት ሆስፒታሎች እየተጨናነቁ መሆናቸውን ከየአካባቢው የሚወጡ ሪፖርቶች ይናገራሉ።
ወደ ስምንት ሚሊየን የሚጠጋ ሰው በኮሮናቫይረስ የተያዘባት ህንድ ትናንት ብቻ ከሃምሣ ሺህ በላይ አዳዲስ ተጋላጮችን የመዘገበች ሲሆን ከስድስት መቶ በላይ ሰው ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዙ ህመሞች ምክንያት በአንድ ቀን ሞቶባታል።
ፈረንሣይ፣ ኢጣልያና ሩሲያም ትናንት የመዘገቧቸው የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ቁጥሮች እስካሁን አጋጥመው የማያውቁ መሆናቸው ተገልጿል።
ከትናንት ጀምሮ እንግሊዝ ለአራት ሣምንት፣ ግሪክ ለሦስት ሣምንት መሉ በሙሉ ዘግተዋል።