No media source currently available
በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወስኖ ቡሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተግባራዊ ያላደረገውን አቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና መብት፤ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በማስፈፀም አቶ ልደቱን ከእስር እንዲፈታ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ትዕዛዝ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ አያሌው የተከሰሱበትን የህገወጥ ጦር መሳሪያ የመያዝ ክስን ዛሬ ምስክር ሰምቷል።