ፕሬዚደንቱ ከአንድ ሳምንት በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ይፋ አድርገውሆስፒታል ተኝተው ከበድ ያለ ህክምና ከተደረገላቸው ወዲህ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸውይሆናል።
ኤቢሲ ኒውስ አስቀድሞ እንደዘገበው ፤ፕሬዚደንቱ ንግግር የሚያደርጉት ዋይት ሃውስ ሰገነት ላይ ሆነው ነው፤ በንግግራቸው ሰለሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፈኞችየሚያስተላልፉት የሕግና ስርዓት ጉዳይ ላይ ያተኮረ መልዕክት ይኖራል።
ፕሬዚደንቱ ዎልተር ሪድ ሆስፒታል ለአራት ቀናት ተኝተው ከታከሙ በኋዋላ ሰኞ ዕለትመውጣታቸው ሲታወስ ከዚያ ወዲህ ሃኪሞቻቸው ጥሩ ይዞታ ላይ እንዳሉ ሲናገሩቆይተዋል።
ሃኪማቸው ዶክተር ሾን ኮንሊ ሃሙስ ማታ በሰጡት ቃል “ የተደረገላቸው ምርመራበጥሩ ይዞት ላይ እንዳሉ ያሳያል፥ ህመማቸው እየተባባሰ እንደመጣ አንድም ምልክትአላገኘንም” ብለዋል፤
ዶክተር ኮንሊ በመቀጠል ፕሬዚደንቱ በቫይረሱ መያዛቸው ከታወቀበት ወዲህ ዛሬቅዳሜ ዐስረኛ ቀናቸው እንደሆነ እና የተደረገላቸውን የተራቀቀ ምርመራ መሰረትበማድረግ ከቅዳሜ ጀምሮ ወደሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ ሙሉ በሙሉ እጠብቃለሁ ብለዋል፡
ያም ሆኖ የህዝብ ጤና ባለሙያዎች “ቸኩለው ህዝባዊ ዝግጅት ላይ መገኘታቸውተገቢ አይደለም” የሚል ጥያቄ አንስተዋል።