በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአንበጣ መንጋ ትግራይ እና አማራን እያስጨነቀ ነው


የውሃ መያዣ ፕላስቲኮች ውስጥ ድንጋይ ጨምሮ በመወዝወዝ ድምፅ በማውጣት አንበጣውን ለማባረር ጥረት እያደረጉ
የውሃ መያዣ ፕላስቲኮች ውስጥ ድንጋይ ጨምሮ በመወዝወዝ ድምፅ በማውጣት አንበጣውን ለማባረር ጥረት እያደረጉ

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን እና በአብዛኛው የአማራ ክልል ምስራቃዊ  ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮችን የአንበጣ መንጋ እያስጨነቃቸው ነው። በከፍተኛ ደረጃ የወረራቸውየአንበጣ መንጋ የደረሰ ሰብላቸውን እያጠፋው መኾኑን አርሶ አደሮቹ ገልፀዋል።

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ራያ ጨርጨር፣ ራያ አዘቦ እና ራያ አላማጣ በተባሉ ሦስት ወረዳዎች ውስጥ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለማባረር በተለያየ መልኩ የተሰባሰቡሰዎች፤ ጥረት ቢያደርጉም የመንጋው ብዛት ከመጠን በላይ በመሆኑ መቋቋም እንዳቃታቸው አርሶ አደሮቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ውስጥ ከ100 በላይቀበሌዎች በሚገኙ የአርሶ አደር ማሳዎች ላይ የአንበጣ መንጋው ከፍተኛ ጉዳትማድረሱ ታውቋል። የደረሰ የማሽላ ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ በመንጋው እንደተወረረባቸው የሚናገሩት አርሶ አደሮቹ፤ ለመከላከል ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዳሉ ተናግረዋል።

በትግራይ እና በአማራ ክልል በተጠቀሱት ቦታዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋው በድምፅ ይሄዳል በመባሉም በፊሽካ፣ የውሃ መያዣ ፕላስቲኮች ውስጥ ድንጋይ ጨምሮ በመወዝወዝ ድምፅ በማውጣት ፣ በመኪና ጡሩንባ እና በሌሎችም ባህላዊ መንገዶች በመሞከር ላይ ቢሆኑም በተሳካ ሁኔታ መንጋውን ለማባረር የተቀናጀ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG