በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

« እንደ መንግስት ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው»-ጥቂት ስለ “እኛ ለእኛ ”የስደት ማህበር


ቤሩት በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ለመገልገል ተራ የሚጠብቁ ኢትዮጵያዊያን
ቤሩት በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ለመገልገል ተራ የሚጠብቁ ኢትዮጵያዊያን

እኤአ በ2018 ዓ.ም የሊባኖስ የስራ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው ሰነድ እንደሚያሳየው በሀገሪቱ በስራ ላይ ከተሰማሩ የውጭ ሀገር ሰዎች ሁሉ የኢትዮጵያዊያን ቁጥር ይልቃል።የሀገሪቱ ህግ በሚፈቅደው መንገድ ታውቀው  የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር  ከ150ሺ እንደሚበልጥም ያሳያል።

ስደተኞች ላይ መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላን ጨምሮ የመንግስት ወገን ምንጮች የተጠቀሰው ቁጥር ላይ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ መካከለኛው ምስራቋ ሀገር ገብተው በመስራት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከተደመረበት ወደ 400ሺ እንደሚጠጋ ይጠቁማሉ።

ወትሮውኑም «ከፋላ» በተሰኘው አሰራር መሰረት ስራ የሚቀጠሩ ኢትዮጵያዊያን ከሚያሰሙት የፍትህ እና የሰብአዊነት ምሬት ጋር በተገናኘ ሊባኖስ ተደጋግማ ተነስታለች።

አሁን ላይ ደግሞ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት በሀገሪቱ እየተንሰራፋ መምጣቱ ሌላ ዓይነት ፈተና በዚያ በሚኖሩት ሁሉ ላይ ደቅኗል።

የሰሩበትን ደሞዝ ከቀጣሪዎቻቸው ማግኘት ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የመንግስታቸውን ጥረት አሊያም «እኛ ለእኛ በስደት» የተሰኘውን ማህበር ዐይነት ግብረሰናይ ተቋማትን እርዳታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈልጓቸዋል።

መቀመጫውን ሊባኖስ እና ካናዳ ውስጥ ያደረገው እኛ ለእኛ የስደት ማህበር የዛሬ 3 ዓመት ገደማ የተቋቋመ ነው።በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ድምጽ እያጎሉ ከመጡ ተቋማት አንዱ የሆነው ማህበሩ ከኮቪድ 19 መቀስቀስ በኃላ የስደተኞችን ፈታኝ ህይወት በተቻለው መንገድ ለማፍካት መሞከሩን የማህበሩ መስራች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግራለች።

የማህበሩ የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴ ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉትን ሆኖም ዕጅ ያጠራቸውን በመርዳት ላይ አተኩሯል።በመላ ዓለም ከሚኖሩ ለጋሾች የሚገኝ ገንዘብን በመጠቀም ለተወሰኑ ስደተኞች ትኬት መግዣ እያዋለም ይገኛል።

የማህበሩ መስራች ባንቺ ይመር መንግስት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሊሰሩት የሚገባውን ተግባር፣ የማህበሩ አባላት በግለሰብ ደረጃ ለማከናወን እየጣሩ ስለመሆናቸው ትናገራለች። ሆኖም አሁን ከሚታየው የድጋፍ መጠን የላቀ ርብርብ እንዲኖር ትሻለች። ኢትዮጵያዊያን ማንነትን ሳይለዩ በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ሊያግዙ እንደሚገባም ታስረግጣለች።

የአሜሪካ ድምጹ ሀብታሙ ስዩም በአሁኑ ጊዚ ካናዳ ምትገኘውን ባንቺ ይመርን በስልክ በማግኘት በማህበሩ ወቅታዊ እንቅስቃሴ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተወሰኑ ጥያቄዎችን አቅርቦላታል።የማህበሩን አመሰራረት በማስታወስ ባንቺ ትጀምራለች።

መልካም ቆይታ ።

« እንደ መንግስት ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው»-ጥቂት ስለ “እኛ ለእኛ ”የስደት ማህበር
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:58 0:00


XS
SM
MD
LG