በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በደህና ሁኔታ እንደሚገኙ ሃኪማቸው አስታወቁ


የፕሬዚዳንቱ ሃኪም ዶ/ር ሾን ኮንሊ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሲሰጡ
የፕሬዚዳንቱ ሃኪም ዶ/ር ሾን ኮንሊ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሲሰጡ

በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጤንነታቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የፕሬዚዳንቱ ሃኪም ዶ/ር ሾን ኮንሊ አስታወቁ። ዛሬ ከሰዓት መግለጫ የሰጡት ሃኪማቸው ፕሬዚዳንቱ ሐሙስ ዕለት የታየባቸው ጥቂት ሳል፣ የአፍንጫ መታፈን እና የድካም ስሜት ዛሬ እንደተቀረፈላቸው ተናግረዋል።

የአሜሪካ ምርጫ ሊደረግ አንድ ወር ገደማ በቀረበት ጊዜበኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው የዩናይትድ ስቴትሱፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ሜሪላንድ ውስጥ ቤተስዳበተባለ አካባቢ በሚገኘው ዋልተር ሪድ የሕክምና ማዕከልተኝተው ክትትል እያደረጉ ነው።

ዛሬ ማምሻውን የፕሬዚዳንቱ የጤንነታቸውን ሁኔታበተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የፕሬዚዳንቱ ሃኪም ዶ/ር ሾንኮንሊ፤ “እኔና የጤና ቡድን አባላቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድትራምፕ በጥሩ የጤነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙየሚያበስረውን ዜና ስንናገር በደስታ ስሜት ነው። ሐሙስዕለት ፕሬዚዳንቱ ትንሽ ሳል፣ የአፍንጫ መታፈን እና የድካምስሜት ነበራቸው ዛሬ ግን ይህ ሁሉ ተቀርፎላቸው ጥሩመሻሻል እያሳዩ ይገኛሉ” ብለዋል።

የፕሬዚዳንቱ ሃኪም ዶ/ር ሾን ኮንሊ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሲሰጡ
የፕሬዚዳንቱ ሃኪም ዶ/ር ሾን ኮንሊ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሲሰጡ

ፕሬዚዳንቱ እና ባለቤታቸው በኮሮረና ቫይረስ መያዛቸውንይፋ ካደረጉ በኋላ ትላንት አርብ በድጋሚ በትዊተር ገፃቸውላይ፤ “በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ብዬ አስባለሁ። ሁላችሁንምአመሰግናለሁ” ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ጤናቸው በጥሩ ሁኔታላይ እንደሚገኝና ነገር ግን የተሻለ ክትትል እንዲያገኙ በሚልሆስፒታል እንዲገቡ መደረጋቸው ተገልጿል።

የፕሬዚዳንቱ ሃኪም ዶ/ር ሾን ኮንሊ ትላንት ለኋይት ሐውስቃል አቀባይ ኬይሊ ማካኒኒ በጻፉት የውስጥ ማስታወሻ “የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጤንነት በደህና ሁኔታ ላይእንደሚገኝ በዚህ ምሽት ሳሳውቅ ደስታ እየተሰማኝ ነው” ካሉ በኋላ “ፕሬዚዳንቱ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ደጋፊየመተንፈሽ መሳሪያ አያስፈልጋቸውም ነገር ግን ስፔሻሊስቶችተማክረው እንዲሰጣቸው የተደረገው የመጀመሪያ ዙር ቴራፒወስደው አረፍ ብለዋል” ብለው ነበር።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ትናንት ከኋይት ሃውስ ወደ ዋልተር ሪድየሕክምና ማዕከል ወደሚወስዳቸው ሄሊኮፕተር ሊሳፈሩ ሲሉእጃቸውን በማውለብለው እና የአውራ ጣታቸውን ምክልትበማሳየት ደህና መሆናቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ትናንት ከኋይት ሃውስ ወደ ዋልተር ሪድ የሕክምና ማዕከል ወደሚወስዳቸው ሄሊኮፕተር ሊሳፈሩ ሲሉ እጃቸውን በማውለብለው እና የአውራ ጣታቸውን ምክልት በማሳየት ደህና መሆናቸውን ገልፀዋል። ።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ትናንት ከኋይት ሃውስ ወደ ዋልተር ሪድ የሕክምና ማዕከል ወደሚወስዳቸው ሄሊኮፕተር ሊሳፈሩ ሲሉ እጃቸውን በማውለብለው እና የአውራ ጣታቸውን ምክልት በማሳየት ደህና መሆናቸውን ገልፀዋል። ።

ፕሬዚዳንቱ ከሄሊኮፕተሩ ላይ ሲወርዱም በእንግራቸው ወደመኪናው ሲሄዱ የታዩ ሲሆን ቃል አቀባይ ኬይሊ ፕሬዚዳንቱከሆስፒታል ሆነው ሥራቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል። በሌላበኩል በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምኋይት ሃውስ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥእራሳቸውን ለይተው በማቆየት ላይ እንደሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG