አዲስ አበባ —
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ዓመት መስቀል አደባባይ አካባቢ በተሠራውና “ሆራ ፊንፊኔ” በተሰኘውየኢሬቼ በዓል ማክበሪያ ቦታ ላይ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜተከብሯል። በበዓሉ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣የኃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መታደማቸውም ታውቋል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የጥሪ ካርድ በያዙ ውስን ተሳታፊዎች ብቻ በዓሉ መከበሩም ታውቋል። በሌላ በኩል በዓሉ በሰላም መጠናቀቁንም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቀዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)