በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ዶናልድና ባለቤታቸው ሜላኒያ በቤታቸው ውስጥ ራሳቸውን ለይተው እንደሚያቆዩ ተናግረዋል


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕና ባለቤታቸው ሜላኒያ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕና ባለቤታቸው ሜላኒያ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ እሳቸውና ባለቤታቸው ኮሮና ቫይረስ እንደያዛቸው በምርመራ መረጋገጡን አስታወቁ ። ቫይረሱ የሚያስከትለው የኮቪድ - 19 ህመም ምልክት ይኑራቸው አይኑራቸው ለጊዜው በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም። ፕሬዚደንቱ የ74 ዓመት ሰው እንደመሆናቸውና በሰውነታቸውም ክብደት የተነሳ ኮቪድ 19 ሊጸናባቸው የሚችሉ ሰዎች ውስጥ የሚፈረጁ ናቸው።

ፕሬዚደንቱ በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለይተው ማቆየት ስላለባቸው ወደየትም ለመጓዝ አይችሉም። ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ተፎካካሪያቸው ከጆ ባይደን ጋር የሚያደርጉትሁለተኛው ክርክር የታቀደው እ.ኤ.አ ለጥቅምት 18 ነበር። ፕሬዚደንቱ እሳቸውናባለቤታቸው ቫይረሱ እንድተገኘባቸው ይፋ ያደረጉት በዋሽንግተን ሰዓት ከሌሊቱ ሰባትሰዓት ሊል ሲል ነው። በትዊተር ገጻቸው" እኔና ቀዳማዊት ዕመቤት ኮቪድ 19 እንደያዝንተረጋጋጡዋል፥ካሁን ጀምረን ራሳችንን ለይተን በመቆየት የማገገም ሂደት እንጀምራለን" ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ ይህን ካሉ ከ11 ደቂቃ በሁዋላ ዋይት ሃውስ ቤተ መንግስት የፕሬዚደንቱ ሃኪም ዶክተር ሾን ኮንሊ መግለጫ አውጥተዋ። ፕሬዚደንቱና ሚላንያ ቫይረሱእንደተገኘባቸው ያረጋገጡት ዶክተሩ በሁኑ ወቅት በደህና ሁኔታ ላይ ናቸው።በዋይትሃውስ መኖሪያቸው ተወስነው ሊያገግሙ ታቅዷል ብለዋል፥ በዚሁ ወቅትም ስራቸውንያለምንም እክል ማከናወናቸውን ይቀጥላሉ ብዬ እጠብቃለሁ ብለዋል ዶክተሩ

የፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕና ባለቤታቸው ን በኮሮና ቫይረስ መያዝ ዜና ተከትሎምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ በትዊተር ባወጡት የመልካም ምኞት መግለጫ " ከኬረን ጋር ሆነን ለውዶቹ ጉዋደኞቻችን ለፕሬዚደንት ትረምፕ እና ለቀዳማዊት እመቤት ሚላንያ ፍቅራችንን እንገልጻለን፥ እንጸልያላቸዋለን ፥ በመላዋ አሜሪካ ከሚሊዮኖች ጋርሆነን በፍጥነት እንድታገግሙና ሙሉ ጤንነታችሁ እንዲመለስ እንጸልያለን፥ እግዚአብሄርፕሬዚደንቱንና ቀዳማዊት እመቤትን ከነቤተሰባችሁ ይባርክ "ብለዋል

የምክትል ፕሬዚደንቱ የፕሬስ ጸሃፊ ዴቪድ ኦማሊ በትዊተር ገጻቸው ባወጡት ቃል ደግሞምክትል ፕሬዚደንቱና ባለቤታቸው ተመርምረው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው መረጋገጡንተናግረዋል። በክሮዌስያ ጉዞ ላይ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ በበኩላቸው ተመርመረው ኮቪድ 19 እንዳልተያዙ አብረዋቸው ለተጓዙ ጋዜጠኞች አረጋግጠዋል።

አስከትለውም “ፕሬዚደንቱና ባለቤታቸው ፈጥነው እንዲያገግሙ ጸሎቴ ነው” ብለዋል።በመጪው ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲው የፕሬዚደንቱ ተፎካካሪ የቀድሞው ምክትልፕሬዚደንት ጆ ባይደንም በትዊተር ገጻቸው ለፕሬዚደንቱና ለቀዳማዊት እመቤት ሚላንያመልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል "እኔና ጂል ፕሬዚደንት ትረምፕና ቀዳማዊት እመቤት ሚላንያ በቶሎ እንዲያገግሙ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን ፥ ለፕሬዚደንቱናለቤተሰባቸው ጤናና ደህንነት እንጸልያለን” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG