ዋሽንግተን ዲሲ —
ከነዚህ ድርጅቶች መሀል ማሽንን በማስተማር የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ወደ እንግሊዘኛ የሚተረጉም መተግበሪያ (አፕ) የፈጠረ 'ልሳን' የተሰኘ ኩባንያ ይገኝበታል። ልሳን በአማርኛ ቋንቋ የተፃፉ ፅሁፎችን ወደ እንግሊዘኛ፣ በእንግሊዘኛ የተፃፉትን ደግሞ ወደ አማርኛ የሚተረጉም መተግበሪያውን ለህዝብ ያቀረበው አሁን በጀመርነው የኢትዮጵያውያኖች አዲስ አመት መግቢያ ላይ ሲሆን በቅርቡ በትግርኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎችም የትርጉምአገልግሎት መስጠት ይጀምራል።
ከካናዳዊ ተጣማሪው ጋር በመሆን ይህን የፈጠራ ስራ ለህዝብ ያቀረበውን የኮምፒውተር ተመራማሪ ወጣት፣ አስመላሽ ተካን ለዛሬ እንግዳችን አርገን ጋብዘነዋል፣ ቆይታውን ያደረገው ከስመኝሽ የቆየ ጋር ነው።