ዋሽንግተን ዲሲ —
ታላቁ የአፍሪካ ጥበብ ሰንደቅ Great African Art Banner የተሰኘው እንቅስቃሴ ለአፍሪካዊያን መነቃቃት እና ብሩህ ተስፋን በስነጥበብ አማካይነት ለመፈንጠቅ በደቡብ አፍሪካዊ እና ዩጋንዳዊ የስነጥበብ ባለሙያዎች አነሳሽነት የተቋቋመ መርሐ ግብር ነው።
መርሐ-ግብሩ በመላው አፍሪካ 55 ኪሎሜትሮች የሚሸፍን ስዕል ስራዎች ለማስተባባር እቅድ ይዟል። ኢትዮጵያዊያንም 1ኪሜ የሚረዝም አውደ ርዕይ ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
ሀብታሙ ስዩም ያነገረው የመርሐ-ግብሩ የኢትዮጵያ አስተባባሪ ሰዓሊ ሰይፉ አበበ ስለ መርሀ-ግብሩ የበለጠ ለመረዳት የሚያግዙ ሀሳቦችን በመቀጠል ያጋራናል።