ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ፣ ከገባበት ጊዜ አንስቶ፣ 166,027 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል። በዩናይትድ ስቴትስ በተከታታይ ከሁልት ሳምንታት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ፣ በቀን በአመካኝ 1,000 ሰዎች እየሞቱ መሆናቸውን ያመለክታል ተብሏል።
በአሁኑ ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ 5.1 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ይገኛሉ። በቫይረሱ ታማሚዎችም ሆነ በሟቾችብዛት፣ ከዓለም ቀዳሚ ቦታ እንድያዘች ነው።
የኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ኦክላንድ ከተማ ላይ፣ በአዲስ መልክ እንቅስቃሴ ለማገድ ያስገደዳቸው፣ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋት፣ እየጨምረ መሆኑ ተገልጿል።
የሰሜናዊትዋ ከተማ ባለስልጣኖች ዛሬ በገለጹት መሰረት፣ 13 አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች ተገኝተዋል። ሁሉም የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው አራት የአንድ ቤሰብ አባላት ጋር የተያያዙ ናችው። አዲስ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 36 ደርሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን፤ 1.6 ሚልዮን የኦካላንድ ከተማ ሕዝብ፣ ካለፈው ማክሰኞ አንስቶ፣ ለሦስት ቀናት ያህል እንቅስቃሴው እንዲገደብ አዘዋል። ከከተማይቱ የሚወጡ ሰዎች ቢኖሩ ለመመለስ ሲባል፣ ፖሊሶች በከተማይቱ ድንበሮች ተመድበዋል። ጥብቅ የሆነ የአካል መራራቅ ደንብንም ደንግገዋል።
በአዲስ መልክ በተነሳው የቫይረሱ መዛመት ምክንያት፣ የሀገሪቱን ፓርላማ የማፍረሱ ጉዳይ፣ እንዲዘገይ ተደርጓል። እ.አ.አ መስከረም 19 ላይ ሊካሄድ የነበረን የምክር ቤት ምርጫ፣ ወደ ማዘግየት ሊያመር ይችላል።
በዓለም ደርጃ 20.6 ሚልዮን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንዳሉ፣ በሞት የተለዩት ደግሞ ወደ 750,000 እንደሚጠጉ ታውቋል። ኒውዚላንድ ግን በቫይረሱ የሚያዙትም ሆነ በሞት የተለዩት ቁጥር፣ ከአለም ያነሱ ከሚባሉት መካከል ነው። ሀገሪቱ 1,589 የኮረና ቫይረስ በሽተኞች ሲኖሯት፣ የሞቱት 22 ስዎች ናቸው ተብሏል።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አንድ ሌላ፣ የኮሌጅ አትሌቶች ኮንፈረንስ፣ በቅርቡ ሊካሄድ የነበረውን፣ የስፖርት ጨዋታ እንደሚያዘገይ አስታውቋል። . The Big East Conference የተባለው ቡድን፣ ከ 11 የትምህርት ቤቶች አባላቱ፣ በጨዋታው የሚወዳደር እንደሌለ ገልጿል።
The Big Ten እና Pac-12 የተባሉት ግዙፎቹ ቡድኖች፣ በወረርሽኙ ምክንያት፣ የውድድሩን ጊዜ እንደሚያዘገዩ ከማስታወቃቸው በፊት፣ ተገምቶ እንደነበር ተዘግቧል።