ዋሽንግተን ዲሲ —
ሊዮን ሙቴሳ የተባሉ የርዋንድ የኮሮናቫይረስ ግብረ-ሃይል አባልና የሰው ልጅ ዘረ-መል ፕሮፌሰር፤ “የሚመረመሩትን ናሙናዎች ቁጥር በመቀነስ የምርመራው ውጤት በአንድ ቀን ውስጥ እንዲገኝ ማድረግ ይቻላል” ብለዋል።
የሂሳብ አያያዝ የመጠቀሙ ዘዴ፣ በአጭር ጊዜ የበዙ ምርመራዎች ለማድርግ እንደሚረዳና ለእያንዳንዱ ምርመራ የሚወጣውን የ50 ዶላር ዋጋን፣ ከግማሽ በላይ እንደሚቀንስ ተመራማሪዎችም ይናገራሉ። ርዋንዳ 300,000 የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግዋ ታውቋል።
ይህን ዘዴ ያፈለቁት በሽታዎችን በሂሳብ ዘዴ የመከላከል ጥበብ ምሑር ዊልፈርድ ኒድፎን ምርመራ የሚያካሂዱት ባለሞያዎች፣ ስህተት እንዳይሠሩ የሚያግዛችው ሶፍትዌር እየሰሩ መሆንቸው ተገልጿል። ኪጋሊ ውስጥ የአፍሪቃ የሂሳብ ሳይንስ ዓለም አቀፍ መረብ የጥናትና ምርምር ስራ አስኪያጅ ናችው።
ርዋንዳ ከ 2,100 በላይ የቫይረሱ በሽተኞች እንዳሏት ታውቋል። በአህጉሪቱ ያነሰ የተረጋገጠ ቁጥር ካላችው፣ የአፍሪቃ ሃገሮች ውስጥ አንዷ ተደርጋ ትታያለች። የዓለም የጤና ድርጅት፣ የርዋንዳን የኮቪድ 19 አያያዝን አሞግሷል።