ዋሽንግተን ዲሲ —
“በተለይም የሚያሳስበን የኮቪድ 19 ወደ ሊባኖስ መመለስ ነው። የ76 ሚልዮን ዶላር ረድኤት ለማግኘት ተማጽኖ ጀምረናል። ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በሚቻለው ሁሉ፣ ሊባኖስን እንዲረዳና ከጎንዋ እንዲቆም እንጠይቃለን” ሲሉ የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት መርኃግብር ቀጠናዊ ሥራ አስኪያጅ ራና ሐጃ ተናግረዋል።
ሦስት ሆስፒታሎች ሙሉ በሙሉ በፍንድታው እንደወደሙ፣ ሦስት ሌሎች ደግሞ በከፊል ሥራ እንደጀመሩ፣ የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ባለሥልጣኖች ገልጸዋል። የሆስፒታል አልጋዎችን በ600 መቀነሱን፣ በይሩት ካሉት 55 የጤና ጣቢያዎች በግማሽ እንደማይሰሩ ባለስልጣኖቹ አክለው ተናግረዋል።
ሊባኖስ ውስጥ 309 አዲስ የኮሮናቫይረስ በሽተኞች እንደተገኙ የጤናው ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሥራ አስኪያጅ፣ ሪክ ብሬናን ገልጸዋል። ሆስፒታሎችም ጭምር ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ማላላታቸውን፣ ባለስልጣኑ ጠቁመዋል።