በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትምህርት ስርዓት መሻሻል ዘረኝነትን ለመዋጋት እንደሚያግዝ ባለሙያዎች ገለፁ


የትምህርት ስርዓት መሻሻል ዘረኝነትን ለመዋጋት እንደሚያግዝ ባለሙያዎች ገለፁ
የትምህርት ስርዓት መሻሻል ዘረኝነትን ለመዋጋት እንደሚያግዝ ባለሙያዎች ገለፁ

ባለፈው ግንቦት ወር ላይ በሚኒያፖሊስ ግዛት በፖሊስ እጅ ውስጥ እንዳለ የተገደለው የጆርጅ ፍሎይድ ሞት ለዘመናት በኖረው ዘረኝነት ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶችንና ዘረኝነትን ለመዋጋት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደአዲስ ቀስቅሷል። አንዳንድ ባለሙያዎች ደግሞ ዘረኝነትን ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ትምህርት ነው ይላሉ። በዚህ ዙሪያ ማክሲም ማስካሎቭ ያጠናቀረውን ሪፖርት ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።

የጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ በአሜሪካ ሁሉም ግዛቶች የተቃውሞ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ባሉበት ውቅት፣ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የአፍሪካ አሜሪካውያንን ታሪክና ባህል ለማስተዋወቅ የተገንባው ሙዚየም በድህረ-ገፅ አማካኝነት 'ስለ ዘር እናውራ' የሚል አስተማሪ ፕሮጀክት ጀምሯል። የሙዚየሙ ተወካይ ካንድራ ፍላናገን እንደሚያስረዱት፣ ፕሮጀክቱ ለድህረ-ገፁ ጎብኚዎች በአሜሪካን አገር ለዘመናት ስለኖረው ዘረኝነትና ከዘረኝነት ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎች ያስረዳል።

"ድህረ-ገፁ በተለይ በአሜሪካ ውስጥ ስለኖረው የዘረኝነት አጭር ታሪክ ይዟል። ዋናው ፍላጎታችን ግለሰቦችና በአጠቃላይ ማህበረሰቡ በዘር ስለተቃኘው ማንነታቸው እንዲያስቡ መርዳት ነው።"

ድህረ-ገፁ የያዛቸው መረጃዎች ለረጅም አመታት በሙዚየሙ ሰራተኞች ሲዘጋጁ የቆዩ መሆናቸውንና በታሪክ፣ ሳይንስና ሳይኮሎጂ ጉዳዮች ላይ ጥልቀት ያላቸው ጥናቶችን ያካተተ እንደሆነ ፋላናጋር ይገልፃሉ።

"ዝምታ አደገኛ ነው። ዝምታ የራሱን መልእክት ያስተላልፋል። ሸፋፍነን እያለፍነውም ሆነ እንደሌለ ቆጥረን የዘር ጉዳይ ጨርሶ የማይነሳ ከሆነ፣ በመነጋገር ልንፈታቸው እንችላቸው የነበሩ ነገሮችን ያጠፋብናል። በዓለም ላይ እየሆነ ያለውን ነገር እንዳናይ ያደረገናል። ነገሮችን እንዴት ተቀብለን ማሰተናገድ እንደምንችልና፣ በምንተዋወቅ ሰዎች መሃል እንኳን ልዩነታችንን አልፈን በአብሮነት መኖር እንዳንችል ያደርገናል። "

ፕሮጀክቱ በድህረ-ገፁ ላይ የሚጠቀሙዋቸው ግብዓቶች ያለውን እውነታ ብቻ የሚያሳዩ አይደሉም። ከኢኮኖሚ አንስቶ በፖሊቲካው፣ ባህልና ትምህርት ዙሪያ በዘር ምክንያት በአሜሪካኖች ህይወት ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮችም መፍትሄ የሚያስቀምጡ መሆኑን ሌላዋ የሙዚየሙ ሰራተኛ አና ሂንድሌይ ይናገራሉ።

"አንድ ተማሪ በትምህርት ቤት ቆይታው በሙሉ የሚነገረው በአንድ ወገን የተቃኘ፣ በነጭ ወንዶች እይታ የሚነገር ታሪክ ነው። እኛ ደግሞ አጥበቀን እየደገፍን ያለነው ታሪኮች ከብዙ አቅጣጫ እንዲታዩ ነው። የአፍሪካ አሜሪካዊ ታሪክ፣ የአሜሪካ ጠቅላላ ታሪክ ነው። "

በሌላ በኩል በሎስ አንጀለስ ከተማ፣ ካሊፎርኒያ ዩንቨርስቲ አስተማሪና በዩንቨርስቲው በመብት ዙሪያ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች አስተባባሪ የሆኑት ጌሪ ኦርፊልድ፣ ዋናው ችግር በአሜሪካ ትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚሰጡት ትምህርቶች ብቻ ሳይሆኑ የተቀረፁበት መንገድም ነው ይላሉ። ኦርፊልድ የሚመሩት ፕሮጀክት በ2006 ባሳተመው ሪፖርት፣ በቀለም የሚከፋፍለው የአሜሪካ ትምህርት ስርዓት ከ1960ዎቹ ጀምሮ ምንም ያክል መሻሻል እንዳላሳየ ያትትታል። ሪፖርቱ ከወጣ 14 አመት ቢሆነውም፣ ሁኔታዎቹ ግን እየተባባሱ ነው ይሄዱት ይላሉ ኦርፊልድ።

"በዋናነት የዘርና የመደብ ችግሮች አሉብን። አሜሪካ ውስጥ ጥቁሮች፣ ላቲኖዎችና የአሜሪካ ዝርያ ያላቸው ተማሪዎች በብዛት የሚማሩት በጣም ድህነት በበዛባቸው ትምህርት ቤቶች፣ ልምድ በሌላቸው አስተማሪዎች፣ ውሱን በሆነ ስርዓተ-ትምህርት ውስጥ ነው። አብረዋቸው የሚማሩዋቸው ተማሪዎችም ብዙ ተወዳዳሪ አይደሉም። ወላጆቻቸውም አቅም የላቸውም።"

ኦርፊልድ የቻርተር ትምህርት ቤቶችና የግል ተቇማት መስፋፋት ለቀለም መከፋፈሉ አስተዋኦ እንዳደረጉ ይናገራሉ። እነዚህ ትምህርት ቤቶች፣ እንደህዝብ ትምህርት ቤቶች ዘርን ሳይለዩ ተማሪዎችን እንዲቀበሉ ወይም የሲቪል ህግ ትምህርቶችን እንዲያስተምሩ አይገደዱም።

"በ1960ዎቹና 70ዎቹ፣ ትምህርት ቤቶች በአንድ ታቅፈው የገንዘብ እርዳታ እንዲደረግላቸውና እንዲሻሻሉ፣ የተለያየ ቀለም ያላቸው ተማሪዎች በተሻለ ትምህርት ቤቶችና ማህበረሰብ ውስጥ ተቀላቅለው መማር እንዲችሉ የሚያደርጉ ፖሊሲዎችን በተከታታይ ይወጡ ነበር። ነገር ግን ጠቅላይ ፍርድቤቱ የበለጠ ፅንፈኛ በሆነ ቁጥር ትምህርት ቤቶቹን እንዳይከፋፍሉ የሚያደርገው እቅድ እየተተወ መጣ።"

ኦርፊልድ በሰብዓዊ መብት እንቅስቃሴዎች ወቅት ተጀምረው ወደነበሩት ትምህርት ቤቶች በቀለም እንዳይከፋፍሉ የሚያደርጉ አሰራሮች መመለስ ያሰፍልጋል፣ ወላጆችም ለልጆቻቸው የሚፈልጉትን ትምህርት ቤት መርጠው ማስተማር እንዲችሉ መደረግ አለበት ብለው ያምናሉ።

የትምህርት ስርዓት መሻሻል ዘረኝነትን ለመዋጋት እንደሚያግዝ ባለሙያዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00


XS
SM
MD
LG