በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አብን፣ ህወሓት ከሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር እንዲሰረዝ ጠየቀ


.
.

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ከሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር መሰረዝ አለበት ሲል አስታወቀ። አብን እዚህ አቋም ላይ የደረሰው ህወሓት ለዓመታት የፈጸማቸው እና አሁንም በመፈጸም ላይ ያሉ ድርጊቶች በአማራ ህዝብ እና ክልል ላይ ብሎም በመላ ኢትዮጵያ ላይ ከደቀነው አደጋ አንጻር እንደሆነ አስታውቋል።

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አማኑኤል አሰፋ በበኩላቸው ፣ ለዓመታት ኢትዮጵያን ለሰላምና ልማት ለማብቃት መስዋዕትነት የከፈለን ፓርቲ ከሰላማዊ ፓርቲነት ይሰረዝ ዘንድ ብሎ መጠየቅ "ክህደት" ነው ብለዋል። ፓርቲውን ለማጥፋት ከሚደረጉ እንቅሳቃሴዎች መካከል አንዱ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ሀብታሙ ስዩም ዝርዝር ጉዳዩን ይዟል።

አብን -ህወሓት ከሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር እንዲሰረዝ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:21 0:00


XS
SM
MD
LG