በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአለም የጤና  ተቋማት  በኮቪድ 19 መዛመት  ምክንያት  መራቆታቸው  ተገለጸ


በአለም ዙርያ ያሉት የጤና ተቋማት በአለም አቀፉ የኮቪድ 19 መዛመት ምክንያት መራቆታቸው ታውቋል። ስለሆነም ሴቶች ከእርግዝናም ሆነ ከወሊድ ጋር በተያያዘ የጤና ችግር ለህልፋት ሊጋለጡ እንደሚችሉ የአለም የጤና ድርጅት ዋና ስረ-አስኪያጅ ዶከተር ቴድሮስ አድሃኖም አስገንዝበዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህዝብ ብዛት አገልግሎት ዋና ስራ አኪያጅ Dr. Natalia Kanem በተናገሩት መሰረት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ ባፊትም ቢሆን በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሴቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ ጥራት ላለው ህክምና ተደርሽነት አልነበራቸውም ብለዋል። ከወረርሽኙ በሁዋላ ደግሞ ለክፋ ሁኔታ መዳረጋቸውን ጠቁመዋል።

እስካሁን ባለው ጊዜ በእናቶች የጡት ወተት ላይ ቫይረስ ባለመገኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን ማጥባት እንዲቀጥሉ አገልግሎቱ እያበረታታ መሆኑን በአለም የጤና ድርጅት የናቶች፣ አዲስ የተወለዱ ህጻናት፣ የልጆች፣ የጎልማሶችና የአረጋውያን ጤና ክፍል ስር አስክያጅ Dr. Anshu Banerjee አስገንዝበዋል።

XS
SM
MD
LG