በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግመል ቤተ-መጽሃፍት፤ከትምህርት ለራቁ ህጻናት አማራጭ መላ


ግመል እና አህያን በመሰሉ እንሳሳት ጀርባ የሚንቀሳቀሰው ቤተ-መጽሃፍት ወደ በርካታ ህጻናት ከንባብ እንዳይርቁ አማራጭ መላ ሆኗል።
ግመል እና አህያን በመሰሉ እንሳሳት ጀርባ የሚንቀሳቀሰው ቤተ-መጽሃፍት ወደ በርካታ ህጻናት ከንባብ እንዳይርቁ አማራጭ መላ ሆኗል።

የዓለም ጭንቀት የሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ህጻናት ከትምህርት ቤቶች እንዲርቁ ምክንያት ሆኗል።

ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ቅጽር ግቢ ውስጥ ብቻ ያገኟቸው የነበሩ ልዩ ልዩ መጽሃፍትን እና መሰል ቁሳቁሶችን እንዳያገኙ በመገደብ በለጋ ዕድሜያቸው ሊያካብቱት የሚገባውን ዕውቀት እየሸረሸረ እንደሆነም ይታመናል።በተለይ ደግሞ ከመሐል ሀገር ርቀው ፣ የአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በሚኖርባቸው ስፍራዎች የሚገኙ ህጻናት ንባብ አጋዥ ቁሳቁሶችን ማግኘት በእጅጉ ይከብዳቸዋል።

ለመሰል ችግሮች መፍትሄ ይሆን ዘንድ የህጻናት አድን ድርጅት «የግመል ቤተ-መጽሃፍት» የተሰኘውን መርሐ-ግብር በአማራጭነት አቀርቧል።

ይህ መርሐ-ግብር ለአለፉት 10 ዓመታት በስራ ላይ እንደቆየ የሚናገሩት የህጻናት አድን ድርጅት የተግባቦት ኃላፊ እና ቃል አቀባይ ህይወት እምሻው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በደቀነው አዲስ ፈተና ውስጥም መርሐ-ግብሩ ህጻናት የሚገኙባቸው ሰፈሮች ድረስ መዝለቅ መጽሃፍትን እያቀረበ እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

በግመል ጀርባ ላይ ተጭነው በርካታ የአርብቶ አደር መንደሮችን ያካለሉት አነስተኛ ቤተ-መጻህፍት ከ20ሺ በላይ ለሆኑ ህጻናት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኝ ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል።

በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተደረገውን ሙሉ ቃለ- ምልልስ ያዳምጡ።

የግመል ቤተ-መጽሃፍት፤ከትምህርት ለራቁ ህጻናት አማራጭ መላ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:07 0:00


XS
SM
MD
LG