በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የገዢው ፓርቲ እጩ የብሩንዲን ምርጫ አሸንፈዋል


የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ እጮ የሆኑት ኤቨሪስት እንዳይሺምዬ ድምፅ ከሰጡ በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያአት ሲሰጡ
የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ እጮ የሆኑት ኤቨሪስት እንዳይሺምዬ ድምፅ ከሰጡ በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያአት ሲሰጡ

የገዢው ፓርቲ እጩ የብሩንዲን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በአብላጫ ድምፅ ማሸነፋቸው እስካሁን ይፋ በሆነው ውጤት እየተነገረ ነው። በሌላ በኩል የተቃዋሚ ፓርቲዎች “የምርጫው ውጤት ተጭበርብሯል” በማለት አቤቱታ እያሰሙ ይገኛሉ።

“ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን” በምሕፃረ ቃል (CENI) በመባል የሚታወቀው የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን፤ የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ እጮ የሆኑት ኤቨሪስት እንዳይሺምዬ 69 በመቶ የሚሆን የመራጭ ድምፅ አግኝተው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ይፋ አድርጓል። በምርጫው ተፎካካሪ ሆነው የተቀረቡት ሲ.ኤን. ኤል (CNL) በመባል የሚታወቀው የዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ እጩ አጋቶን ሩዋሳን ደግሞ 24 በመቶ ድምፅ ብቻ በማግኘታቸው ምርጫውን ተሸንፈዋል ብሏል - ኮሚሽኑ።

በሌላ በኩል ብሔራዊ ፓርቲ ከሆነው “ኢፕሮና” እጩ ሆነው የቀረቡትና አሁን በስልጣን ላይ የሚገኙት የአገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋስቶን ሲንዲሞ ደግሞ ሁለት በመቶ ድምፅ ብቻ በማግኘት በምርጫው ውጤት የኋለኛው መስመር ላይ ተቀምጠዋል። ቆጠራው የተጭበረበረ መሆኑን በመግለፅ ውጤቱ ይፋ እንደተደረገ ተቃውሞ ያቀረበው የCNL ተቃዋሚ ፓርቲ ቃል አቀባይ ቴራንስ ማኒራንቦና ለአሜሪካ ድምፅ የመካከለኛው አፍሪካ ቃ`ንቃ` አገልግሎት ሲናገሩ፤ ፓርቲያቸው እጩ አድርጎ የመረጣቸው አጋቶን ሩዋሳን ምርጫውን ማሸነፋቸውን የሚጠቁም የራሳቸው የቁጥር መረጃ እንዳላችቸው ተናግረዋል።

“በብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን (CENI) የተነገረው ውጤት የሕዝቡን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ እንዳልሆነ የተለያዩ ሐቅን መሰረት ያደረጉ መረጃዎች አሉን። በመራጮች የተሰጡት ድምፆች እንደገና እንዲቆጠሩ አግባብነት ያለውን መንገድ ተከትለን እንጠይቃለን” ብለዋል - ቃል አቀባዩ።

የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ እጮ የሆኑት ኤቨሪስት እንዳይሺምዬ ድምፅ ሲሰጡ
የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ እጮ የሆኑት ኤቨሪስት እንዳይሺምዬ ድምፅ ሲሰጡ

የብሩንዲን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ከተነገረው ኤቨሪስት እንዳይሺምዬ በኩል ተቃዋሚዎች እያነሱት ስላለው ቅሬታ የተሰማ ምላሽ የለም። በሌላ በኩል ግን የአገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋስቶን ሲንዲሞ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ለአሸናፊው የእንኳን ደስ አሎት መልዕከት አስተላለፈዋል። አያይዘውም የምርጫውን ውጤት ያሸነፉት ኤቨሪስት እንዳይሺምዬ የሁሉም ብሩንዲያዊያን መሪ እንዲሆኑ እንጠይቃለን ብለዋል።

ገዢው ፓርቲ ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በተጨማሪ 72 ፣ ተቃዋሚ ሲ.ኔ.ል 27 እንዲሁም ብሄራዊ ፓርቲ ኢፕሮና ደግሞ አንድ የፓርላማ መቀመጫዎችን አግኝተዋል።

የመጨረሻው ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው በመጪው ማክሰኞ ሲሆን በምርጫው ውጤት ላይ ተቃውሞ ያለው የትኛውም ፓርቲ ተቃውሞው ለማቅረብ 10 ቀናት አላቸው። በምርጫው ውጤት ማሸነፋቸው የተነገረው የገዢው ፓርቲ አባል ኤቨሪስት እንዳይሺምዬ አገሪቱን ለ15 ዓመታት ያስተዳደሯትን ፕሬዚዳንት ንክሩንዚዛ ይተካሉ ተብሏል።

XS
SM
MD
LG