በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

1 ሺህ 441ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በመላው ኢትዮጵያ ሲከበር ውሏል


ፎቶ - ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፌስ ቡክ ገፅ ላይ የተወሰደ
ፎቶ - ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፌስ ቡክ ገፅ ላይ የተወሰደ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የኢድ አልፈጥር በዓልን ሁሉም በየቤቱ እንዲያከብር ቀደም ብሎ ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት አብዛኛው የእምነቱ ተከታይ ዛሬ በዓሉን በየቤቱ ሆኖ አክብሮታል።

በሌላ በኩል ርቀታቸውን የጠበቁ የኃይማኖቱታላላቅ መሪዎች በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው አንዋርመስጅድ በተለያዩ ሥርዓቶች ተከብሯል። ሥነ ስርዓቱምበቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍ ተደርጓል።

በዚህ የበዓል አከባበር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከልጥንቃቄ እንደሚገባ መክረዋል።

አያይዘውም ሕዝበ ሙስሊም በረመዳን ወርም ኾነ ከዚያበፊት ይፈፅማቸው የነበሩ በጎ ተግባራትን በመቀጠልናከመንግሥት የሚተላለፉ መመሪያዎችን በመከተል ጥንቃቄእንዳይለየው መክረዋል። በአጠቃላይ በዓሉ ኃይማኖታዊሥርዓቱን ጠብቆ በመላ አገሪቱ ተከብሮ ውሏል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳንለ1441ኛው የኢድ - አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

XS
SM
MD
LG