በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው


በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከ4048(ከአራት ሺሕ አርባ ስምንት)  ሰዎች ከተወሰደው ናሙና በተገኘው የምርመራ ውጤት መሰረት 88 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።  

የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር እና የኅብረተሰብ ጤናኢንስቲቲዩት በየዕለቱ በሚያወጡት የ24 ሰዓት የምርመራውጤት የጋራ መግለጫ መሰረት በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያበቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 582 ደርሷል።

የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው 88 ሰዎች በሙሉኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፤ 51 ወንዶች 37 ደግሞ ሴቶች ናቸው።ከስምንት እስከ 75 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙምናቸው። በዛሬው የምርመራ ውጤት ቫይረሱ የተገኘባቸው 73 ሰዎች በአዲስ አበባ የተመረመሩ ናቸው። ስምንት ሰዎችከትግራይ፣አራት ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፣ አንድ ከሐረሪ ክልልሁለት ደግሞ የድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪዎች ናቸው።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫመሰረት፤ በአጠቃላይ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 55 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰውጋር ግንኙነት የሌላቸው ሲሆኑ 13 ሰዎች ደግሞ የውጭ የጉዞታሪክ ያላቸው ናቸው። ቀሪ 20ዎቹ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋርየታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ናቸው።

“የላቦራቶሪ ምርመራ ናሙናዎቹ ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭከሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁምበአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነነው።” ያለው የዛሬው የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓት መግለጫእስካሁን ለ81 ሺህ 10 ሰዎች ምርመራ መደረጉን እና 582 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ጠቁሟል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 423 ሰዎች ሕክምና እየተከታተሉሲሆን፣ 152 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል። በኢትዮጵያአምስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት ሕይወታቸውአልፏል። መጀመሪያ ላይ በቫይረሱ የተያዘው ጃፓናዊውንጨምሮ ሁለት ሰዎች ወደ አገራቸው ጃፓን ተመልሰዋል።

የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር እና የኅብረተሰብ ጤናኢንስቲቲዩት በመግለጫቸው ማጠቃለያ ኅብረተሰቡ ከጤናሚኒስቴር የሚወጣውን መመሪያ በመከተለል ጤናውንእንዲጠብቅ መክረዋል።

XS
SM
MD
LG