በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ ስጋትና የፋሲካ በዓል ፀሎት


የኮሮናቫይረስ ስጋትና የፋሲካ በዓል
የኮሮናቫይረስ ስጋትና የፋሲካ በዓል

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸውና በነገው ዕለት የሚከበረው የፋሲካ በአል በኮሮናቫይረስ ምክንያት ድምቀቱ ቀንሷል። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚያዚያ 8 ባወጣው መግለጫ በቤተሰብ መካከል የሚካሄድ የአካል መጠያየቅ እንዳይኖር የቅድመ ጥንቃቄ መመሪያ አስተላልፏል። ከዛም በተጨማሪ የሀይማኖት ተቇማት ህብረተሰቡ ከበሽታው እንዲጠበቅ ምዕመናን ከቤታቸው ሆነው በዓሉን እንዲያከብሩ መመሪያዎችን አውጥተዋል።

የዘንድሮ የፋሲካ በዓል ሀይማኖታዊ አከባበር ምን እንደሚመስል ባልደረባችን ስመኝሽ የቆየ የሀይማኖት አባቶችንና የእምነቱን ተከታዮች አነጋግራ የሚከተለውን አጠናክራለች።

የኮሮናቫይረስ ስጋትና የፋሲካ በዓል ፀሎት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:43 0:00


በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነው ዩሀንስ መኮንንና ቤተሰቦቹ በጋራ ተሰባስበው በድምቀት ከሚያከብሩት በዓል አንዱ ፋሲካ ነበር። ከበዓሉ ዕለት ቀደም ብሎ በኃይማኖታዊ ሥነ- ስርዓት ከሚከበረው የስግደትቀንጀምሮ ትንሳኤ የቤተሰብ በዓላቸው እንደሆነ ይናገራል።

"ብዙጊዜገዳማትእሄዳለሁ።ቤተሰቦቼ፣ልጆቼእናባለቤቴሆነንገዳማትእናከብራለን።ገዳማትመሄድየማንችልባቸውሁኔታዎችቢፈጠሩበቅርባችንባለውቤተክርስቲያንሌሊትከአባቶቻችንጋርቅዳሴተካፍለንወደቤታችንእንመለሳለን።በዚህመልኩነበርየምናከብረውየእስካሁኑን።"

የዘንድሮየፋሲካበዓልግንለዩሃንሰናለቤተሰቡእንደወትሮውአይሆንም።የዛሬአራትወርገደማበቻይናውሃን ከተማ የጀመረውናበአጭርጊዜ መላውን ዓለም አዳርሶ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነውየኮሮናቫይረስበኢትዮጵያመገኘት፣እንዲሁምበቫይረሱየተያዙሰዎችቁጥርመጨመርንተከተሎየኢትዮጵያኃይማኖታዊተቋማትምዕመናንወደቤተክርስቲያንከመሄድእንዲቆጠቡመመሪያን አስተላልፈዋል። ይህ ለዩሃንስ እና ቤተሰቡ ልብ ሰባሪ ቢሆንም መመሪያውን ግንተግባራዊ እንደሚያደርገው ያረጋግጣል።

“በጣም ልብ ይሰብራል። በጣም ያሳዝናል። ባልመድነው መልኩ፣ በዚህ እድሜዬ በሙሉ አንድም እንደዚህ አይነት ነገር ገጥሞኝ አያውቅም። በሕይወታችን፣ ምናልባትም ለቀሪው ትውልድ የምንነግረው አጋጣሚ ነው ብዬ ነው የማስበው። ግን ደግሞ ለቤተክርስቲያን ስንል፣ ለአባቶቻችን ስንል፣ ራሳችንንና ቤተሰባችንን ለመጠበቅ ስንል የአባቶችን ትእዛዝ ተቀብለናል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰጠው የአስቸኯይ ግዜ አዋጅ አውጇል። በቤተ እምነቶችም ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው ውሳኔ መሰረት በየቤታችሁ ጸልዩ ስለተባለ፣ እንደ ዜጋ የሀገሪቱን ህግ አከብራለሁ፣ እንደ አንድ ምዕመን የሲኖዶሱን ውሳኔ፣ የአባቶቼን ውሳኔ አከብራለሁ። ስለዚህ በቤቴ ከቤተሰቦቼ ጋር ሆኜ እናሳልፋለን ብዬ ነው እየተዘጋጀሁ ያለሁት።”

ምንምእንኳንቤተክርስቲያናትህብረተሰቡንከወረርሽኙለመጠበቅምዕመናን በየቤታቸው እንዲፀልዩመመሪያዎችንቢያወጡምአሁንምግን ሰዎችወደቤተክርስቲያናትመሄድንአላቁዋረጡም።ያለፈውእሁድበተከበረውየሆሳዕናበዓልላይምየምዕመናንበብዛትወደቤተክርስቲያንመሄድናበአንዳንድቦታዎችየተፈጠረውመጨናነቅከፍተኛ ስጋትንፈጥሯል።ስጋቱንም ለመቀነስ በኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶቤተክርስቲያንቅዱስሲኖዶስውሳኔየተቋቋመው የተስፋልኡክአብይግብረኃይልየቤተክርስቲያናትንበርከመዝጋትአንስቶሌሎችእርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።የግብረሀይሉፀሀፊቀሲስሙሉቀንብርሀኑበተለይበፋሲካበአልዙሪያአየተደረጉስላሉጥንቃቄዎችሲያስረዱ፣

"በበአሉቅዱስሲኖዶስምእመናኑቤታቸውሆነውእንዲፀልዩ፣እንዲፆሙ፣እንዲሰግዱአዟል።በዛመሰረትምዕመናኑቤታቸውነውያሉት።በየአብያተክርስቲያኑ ውስንካህናትአገልግሎቱንእንዲፈፅሙ፣እንዲቀመጡባዘዘውመሰረትቅዳሴውም፣ኪዳኑም፣ማህሌቱምበአጠቃላይየቤተክርስቲያኑንአገልግሎት፣ከማማቱበፊትየነበረውን፣አሁንከማማትላይምያለውንምአገልግሎትየሚከውኑካህናትተመድበውእየተከወነነውያለው።ወደቤተክርስቲያንየሚመጣአይኖርም።”

ቀሲስሙሉቀንአያይዘውቤተክርስቲያኗየምታካሂደውንሥርዓትመከታተልለሚፈልጉናለሚሰግዱምዕመናንበየቤታቸውሆነውመከታተልየሚያስችላቸውሁኔታዎችእንደተመቻቹላቸውያሰረዳሉ።

"ከቤታቸውሆነውአገልግሎቱንእንዲከታተሉወይምየሚሰግዱትምአሁንባሉትቴሌቭዥኖችቀጥታእየተላለፈስለሆነበተለይባላገሩቴሌቭዥንጣቢያሰሞነህማማትንከጠዋትጀምሮስርአቱስከሚያልቅድረስበቀጥታእያስተላለፈስለሆነ ነው።ስለዚህቴሌቭዥናቸውንእየተከታተሉ፣ስርአቱንእየተከታተሉቤታቸውሆነውእንዲሰግዱነውየተወሰነው።"

ሌላው የፋሲካበዓልከሚከበርበት አንዱ የሆነውየኢትዮጵያወንጌላውያንአብያተክርስቲያናትኅብረትፕሬዝዳንትወንጌላዊፃዲቁአብዶ፣በሥራቸውያሉትከ65 በላይቤተእምነቶችወረርሽኙንለመቆጣጠርእየወሰዱትስላሉትእርምጃሲያስረዱ፤መንግሥትበአስቸኳይጊዜዐዋጁከአራትሰውበላይመሰብሰብመከልከሉንተከትሎምዕመናንወደቤተክርስቲያናትእንዳይመጡተደርጓልይላሉ።

"በሶሻል ሚዲያ፣ የሳተላይት ሚዲያዎች፣ ቻናሎች፣ የዌብ ሳይት ቻናሎች እንጠቀማለን። ሁሉንም መጠቀም አንችልም ግን ከተወሰኑት በጋራ እየሰራን ለህዝቡ መልክቶች እየተላለፉ ነው። አሁንም በአሉን አስመልክተን እሁድ ጠዋት ቤተክርስቲያናት በተለያዩ ቻናሎች መልእክታቸውን ለህዝባቸው ያስተላልፋሉ።በዚህ አይነት መልኩ ነው ለመድረስ ሙከራ እያደረግን ያለነው። ስለዚህ ማንኛውም ሰዉ ለምሳሌ ጎረቤቶች ሊኖሩ ይችላሉ ወይም አንድ ቤተሰብ በነዚህ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቅሞ በአሉን በቤቱ እንዲያከብር እና ከጎረቤት ደግሞ ለሌለው እንዲያካፍል ነው ኢንከሬጅ የምናደርገው።"

የካቶሊክቤተክርስቲያንምበበኩሏቫይረሱወደኢትዮጵያመግባቱከተረጋገጠበትጊዜአንስቶበበሽታውዙሪያያሉመረጃዎችንሰዎችእንዲያውቁናመንግሥትያወጣቸውመመሪያዎችንእንዲያከብሩከማስተማርአንስቶየእምነትተቋማትሥራቸውንአቋርጠውምዕመናንበቤታቸውሆነውእንዲፀልዩስታደርግ ቆይታለች።የፊታችንእሁድለሚከበረውየፋሲካበዓልምሆነ ከዚያ በሁዋላ ካህናትበዝግቤተክርስቲያናትምዕመናትበሌሉበትብቻቸውንይቀድሳሉ። ምዕመናኖችምበየቤታቸውሆነውበተለያዩየቴሌቭዥንጣቢያዎችይከታተላሉያሉንአባተሾመፍቅሬየኢትዮጵያካቶሊካዊትቤተክርስቲያንየጳጳሳትጉባኤዋናጽ/ቤትዋናጸሐፊናቸው።

“በሁሉምቤተክርስቲያኖቻችንአንድአንድ፣ሁለትሁለትካህናትሆነውየፋሲካቅዳሴይቀድሳሉ።ሕዝብበሌለበት።ቴሌቭዥንየሚተላለፈውከአንድቤተክርስቲያንብቻነው።ሌሎቹቤተክርስቲያኖችዝግአይደሉም ነገርግንምዕመናንግንወደቤተክርስቲያንአይመጡም።ካህናትየህዝቡንፀሎት፣የህዝቡንንሰሀ፣የህዝቡንይቅርታተሸክመውፀሎታቸውንወደእግዚአብሄርያደርሳሉ።”

አባተሾመጨምረውዘንድሮየሚከበረውየፋሲካበአልበቤተሰብመሀልበአብሮነትየሚከበርአይደለምይላሉ።

“ቤተሰብብቻውን በቤተሰቡውስጥበታላቅጥንቃቄየሚያከብረውነው።ዘመድየሚጠያየቅበትበአልአይደለም።ይሄዘመንአልፎሲመጣበጋራየምናመልክበት፣በጋራቤተክርስቲያንሄደንሀሌሉያብለንየምንዘምርበት፣ቤተሰብተጠራርተንበጋራየምናከብርበትጊዜሩቅአይደለምብለንተስፋእናደርጋለን።ለአሁኑግን፣ለዘንድሮውግንየትንሳኤበአላችንበልባችንየምናከብረውነው።በቤታችንውስጥየምናከብረውነው።

ቀሲስ ሙሉቀንም ይሄ ወረርሽኝ ያልፋል ሲሉ የራሳቸውን ምክር ያለግሳሉ።

“ለሚያልፍ ወረርሽኝ የማያልፍ ጠባሳ ቤተክርስቲያኗ ላይ ጥሎ እንዳይሄድ ነው ውሳኔ የተወሰነው እና ምዕመናን ቤታቸው ሆነው መስገድ ይችላሉ። እግዚአብሄር መንፈስ ነው። እግዚአብሄር በሁሉም ቤት አለ። እግዚአብሄር ከኛ ጋር ነው። ስለዚህ ሁለትም ሶስትም ሆናችሁ በተሰበሰባችሁበት እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ ነውና ያለው፣ በቤታችን ባለችው ቤተክርስቲያን ስርዕት አምልኮው ሳይጏደልብን፣ ስርዐተ ፀሎቱ ሳይጏደልብን፣ እየሰገድን፣ እየፆምን አብዝተን እየፀለይን ይህን ወቅት ይህን ወረርሽኝ ማሳለፍ አለብን።”

ሁሉምየኃይማኖትአባቶች በተለይ በበዓላት ሰሞን ራስን መጠበቅ፣የኃይማኖት ተቋማት፣የጤናጥበቃ ሚኒስቴር፣የሕክምና ባለሞያዎችናየዓለምየጤናድርጅትየሚያወጧቸውንመመሪያዎችንማክበርትውልድንናሀገርንመጠበቅነውይላሉ። የበዓል ግዢዎች በሚፈፀሙበትም ወቅትም ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ይመክራሉ። ከበዓሉ ውጪም ቢሆን ይህ ጊዜ እስኪያልፍ በየቤታችሁ ሆናችሁ ፀልዩም ሲሉም ያሳስባሉ።

XS
SM
MD
LG