በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተሰብስበው «ሺሻ» ሲያጨሱ ነበር የተባሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ


የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ሰበብ አድርገው ወንጀል የሚፈጽሙን እየተቆጣጠረ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ሰበብ አድርገው ወንጀል የሚፈጽሙን እየተቆጣጠረ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ሰበብ አድርገው የሚፈጠሩ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴዎችን መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት የከተማው የፖሊስ አባላት ራሳቸውን ከቫይረሱ ከመጠበቅ ሳይቦዝኑ ሁኔታውን ሰበብ አድርገው ዋጋ የሚያንሩ የንግድ ቤቶችን እየተቆጣጠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

« ሺሻ» ማስጨሻ ቤቶችን የመሰሉ ለቫይረሱ ስርጭት የእጅ አዙር አስተዋጽኦ ያላቸውን ስፍራዎች በመዝጋት ሂደት ውስጥ የተገኙ ከ100 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

ኮማንደር ፋሲካ በማቆያ ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ፣በሚፈጠር መተፋፈግ ለኮሮና ቫይረስ እንዳይጋለጡ ጥንቃቄ እየተደረገ ስለመሆኑም ተጠይቀዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ።

ተሰባስበው “ሺሻ” ያጨሱ ነበር የተባሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:34 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG