በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች የቅንጅት የፀጥታ ኃይል ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሰማራ ታወቀ


ከአማራ ክልል በቀረበው ጥያቄ መሰረት በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች የቅንጅት የፀጥታ ኃይል ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሰማራ ታወቀ።
ከአማራ ክልል በቀረበው ጥያቄ መሰረት በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች የቅንጅት የፀጥታ ኃይል ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሰማራ ታወቀ።

በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋትና አካባቢውን ወደ ቀደመው ሰላም ለመመለስ፤ የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን ጣልቃ ገብቶ እንዲያስተካክል ለፌዴራል መንግሥት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የፌዴራል የፀጥታ ኃይል መከላከያን ጨምሮ ማንኛውንም ሕጋዊ እርምጃ ወስዶ ቀጠናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሟላ ሰላም እና መረጋጋት እንዲያሸጋግር መመሪያ መተላለፉን የአማራ ክልል ደኅንነትና የጸጥታ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ማምሻውን ባወጣው ባለ 11 ነጥብ መግለጫ በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች፣ በጎንደር ከተማ እንዲሁም በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ማንነትን ሽፋን በማድረግ ባለፉት አምስት ዓመታት የዘለቀው የጸጥታ መደፍረስ ለሰው ህይዎትና ለንብረት ጥፋት ምክንያት ሆኖ መቀጠሉን አስታውሷ።

ጉዳዩን ሕግን በተከተለ አሠራር መፍታት እየተቻለ በኢ - ሕገ መንግሥታዊ እንቅስቃሴ አካባቢውን ለግጭትና መዳረጉን በውጤቱም ከፍተኛ ቀውስ መከሰቱን የሚያወሳው የመግለጫው ሐሳብ አጠቃላይ ጉዳዮቹ በስፋይ ይዘረዝራል።

ከመስከረም 15/2012 ዓ.ም ጀምሮም በሰው ህይዎትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በመጠቆም ይህ ጉዳት እንዳይቀጥል የአካባቢው ሰላም በዘላቂነት የአማራ ክልል መንግሥት ለፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን ጣልቃ ገብቶ እንዲያስተካክል ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የፌዴራል የፀጥታ ኃይል መከላከያን ጨምሮ ማንኛውንም ህጋዊ እርምጃ ወስዶ ቀጠናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሟላ ሰላም እና መረጋጋት እንዲያሸጋግር መመሪያ መተላለፉን መግለጫው ይዘረዝራል።

የምክር ቤቱ መግለጫ እንደሚለው፤ የተላለፈውን መመሪያ በመከተል የክልሉ የፀጥታና ደኅንነት ካውንስል በማዕከላዊ፣ በምዕራብ ጎንደር፣ በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር እና በጎንደር ከተማ የተደረጉ ክልከላዎችን ዘርዝሮ ያስቀምጣል።

በዚም መሰረት፤ “ማንኛውም የኃይል እንቅስቃሴን የኃይል እርምጃ በመውሰድ የሰው ህይወትና ንብረትን ከአደጋ ማዳን፣ በድርጊቱ ላይ የተሳተፉትን በኃይል መቆጣጠር፣ ለህግ ማቅረብ፣ ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃን በመውሰድ የኃይል ተግባርን ፍፁም እንዳይቀጥል ማድረግ” ከተግባራቱ መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ያሉትን ጥያቄዎች በጠረንጴዛ ዙሪያ ከመፍታት ውጪ ምንም ዓይነት ምርጫ እንደሌለ በመግለጫው ክፍል ተጠቅሷል።

“ማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን በቀጠናው ላይ ለሚደረገው የፀጥታ ኃይል ስምሪት የመተባበር፣ ወንጀለኛን አሳልፎ የመስጠትና የአከባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ድጋፍ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡” የሚለው የመግለጫው ሦስተኛ ነጥብ ደግሞ “ይህንን የሚያደናቅፍ ማንኛውም ተግባር በህጋዊ እርምጃ የሚስተካከል ይሆናል፡፡” ሲል ያጠናክራል።

የትጥቅ አያያዝን በተመለከተም “በግልፅ በታወቁ የፀጥታ ኃይሎች ከተያዙት ትጥቅና መሳሪያ ውጪ በተጠቀሱት የክልሉ ዞኖች ላልተወሰነ ጊዜ ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለና የሚወረስ ይሆናል፡፡” ሲል አስፍሯል።

በአጠቃላይ በመግለጫው የሰፈረው በተጠቀሱት አካባቢዎች ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግና በማንኛውም ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ነው። የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅም ሁሉም አካል ተባባሪ እንዲሆን ምክር ቤቱ ጠይቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG