በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቦኮ ሃራም ምክኒያት በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች እና ፍልሰተኞች ችግር ላይ ናቸው


የቦኮ ሃራም ታጣቂ ቡድን ጥቃት ተጠናክሮ እና ተደጋግሞ በመቀጠሉ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ምስራቅ ኒጀር ስደተኞች እና ፍልሰተኞች በእጅጉ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ተቋም ተናገረ፡፡

እንደ ተቋሙ ማብራሪያ ባለፈው ወር ብቻ መሰረቱን ናይጄሪያ ባደረገው የቦኮ ሃራም ቡድን ጥቃት፣በኒጀር ድንበር ገደማ 88 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ 18000 የሚሆኑ ሰዎች ሸሽተው ከተጠለሉበት ስፍራ ለሁለተኛ እና ሶስተኛ ጊዜ ቤት ንብረታቸውን ትተው እንዲፈናቀሉ ምክንያትም ሆኗል፡፡

ለነፍሳቸው የሳሱት ወገኖች ዲፋ ወደ ተባለችው ከተማ በብዛት እየተመሙ ስለመሆኑ የተነገረ ሲሆን ፣በከተማዋ ተጨማሪ መጣበብ እንዳይፈጠር ተሰግቷል፡፡

ከአውሮጳዊያኑ 2015 ጀምሮ ሩብ ሚሊየን የሚያህል፣ ከቦኮ ሀራም ጥቃት የሸሹ ሰዎች በኒጀር ዲፋ ከተማ ተጠቅተው እንደሚኖሩ ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG