በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ትራምፕ የአካባቢ ጥበቃ መ/ቤት ደንብን የሚቀይር ትዕዛዝ ፈረሙ


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግብፁን ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲን ለመቀበል እየተጠባበቁ የተነሱት ፎቶ ነው
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግብፁን ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲን ለመቀበል እየተጠባበቁ የተነሱት ፎቶ ነው

የዮናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የሀገሪቱን ሃይል አመንጪ ተቋማት የሚመለከቱ ሁለት የበላይ ትዕዛዞችን አስተላለፉ፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲያስፈጽማቸው የተፈረሙት ትዕዛዞች፣ በጠረፍ ግዛቶች ጠንካራ ህግ ሳቢያ የዘገዩ የጋዝ፣ድንጋይ ከሰል እና ነዳጅ ማምረት ስራዎችን ለማፈጠን የታለሙ ናቸው ተብሏል፡፡

ቀደም ብለው የነበሩ ደንቦችን “ጊዜያቸው ያለፈ፣ግርታ የሚፈጥሩ እና መተማመኛ የማይሰጡ”፣ሲሉ የተቹ አንድ ከፍተኛ አስተዳደራዊ ባለስልጣን ፣“የግዛቶችን ሃይል እየነጠቅን አይደለም፣ሆኖም የግዛቶቹ ርምጃ ከህጉ ዓላማ ጋር ይጣጣም ዘንድ እየጣርን ነው ፡፡”ስለማለታቸው ሮይተርስ ዘገቧል፡፡

በከፊል ከሚቀየሩ ደንቦች መካከል አንዱ፤ የየግዛቱ መንግስታት አካባቢ ጥበቃን ምክንያት በማድረግ የዘርፉ ግንባታዎች እንዲዘገዩ ለማድረግ ስልጣን የሚሰጣቸው ‘የአሜሪካ የንጹህ ውሃ ህግ’ ነው፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች አዳዲሶቹን ትዕዛዞች ‹‹ትልልቅ ነዳጅ አምራች ድርጅቶችን ለመጥቀም የተረቀቁ ናቸው ›› ሲሉ ተቃውመዋቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG