ዋሽንግተን ዲሲ —
እጅግ ተቀራራቢ በነበረው የእስራኤል የፓርላማ ምርጫ ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ፣ ሀገሪቱን ለ5ኛ ጊዜ ለመምራት የሚችላቸውን ድምጽ ሳያገኙ እንዳልቀሩ እየተነገረ ነው፡፡
እስከ አሁን 97 በመቶው የድምጽ መስጫ ሳጥኖች የተቆጠሩ ሲሆን፣ ኔታኒያሁ የሚመሩት የቀኝ ክንፍ ሊኩድ ፓርቲ እና ተቀናቃኛቸው የቀድሞ የጦር አለቃ ቤኒ ግራንዝ የሚመሩት የማዕከላዊነት ሰማያዊ እና ነጭ ፓርቲ እኩል ድምጽ አግኝተዋል፡፡
ሆኖም ሊኩድ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመቀናጀት በመቻሉ፣ 120 ወንበሮች ያሉትን የእስራኤል ብሄራዊ የህግ አውጪ ምክር ቤት 65 መቶኛ ለመቆጣጠር እንደሚቻለው እየተነገረ ነው፡፡
ኦፊሳላዊ ውጤቱ ይፋ ባይደረግም ፣ኔታኒያሁ የፓርቲያቸውን ድል በእጅጉ የላቀ ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡
‹‹ሀገረ እስራኤል አሁንም በድጋሜ ለ5ኛ ጊዜ ስለመረጠኝ የላቀ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ከደስታውም ባሻገር የላቀ መተማመኛ ሆኖኛል፡፡እነግራችለሁ፣ ይህ ያልጠበቅኩት ድል ለእኔም ለእናንተም ዋስትና ሰጥቶናል፡፡ይሄን ያህል ብዙ ወንበር ለማሸነፍ የቻልነው መቼ ነበር? አላስታውስም፡፡›› ብለዋል፡፡
የእስከ አሁኑ ግምት ከጸና ቤኒያሚን ኔትናሁ እስራኤልን ለብዙ ዓመታት የአስተዳደሩ መሪ ይሆናሉ፡፡