በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ለስድስት ወራት ተግባራዊ እንደሚደረግ መከላከያ ሚኒስትሩ ገለፁ


የመከላከያ ሚኒስትሩና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ
የመከላከያ ሚኒስትሩና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ

በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በተሰጠው ማብራሪያ፤ ዐዋጁ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ ለቀጣይ ስድስት ተግባራዊ ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል። ዐዋጁ በሁሉም የአካባቢው ክፍሎች እንደሚተገበርም ተናግረዋል።

ለጋዜጠኞች የተሰጠው መግለጫ “ከብሔራው የደህንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ” የሚል ሲሆን፤ መግለጫውን የሰጡት ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትሩና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ናቸው። ዐዋጁ ለማስፈፀም አዲስ ኮማንድ ፖስት እንደሚቋቋም ተናግረዋል።
በዐዋጁ መሰረት የሚደረጉትን ክልከላዎችም አብራርተዋ። “ማንኛውም በሁከትና ብጥብጥ ማድረግ፣ በሕዝቦች መካከል መጠራጠርን እና መቃቃርን የሚፈጥር፣ ይፋዊ የሆነ የድብቅ ቅስቀሳ ማድረግን፣ ጹሑፍ ማዘጋጀትን እና አትሞ ማሰራጨትን፣ ትእይንት ማሳየትን፣ በምልክት መግለፅን ወይም መልዕክትን በማንኛውም ሌላ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድርገን ይከለክላል።” ብለዋል።
አዲስ የሚቋቋመው ኮማንድ ፖስቱ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፤ “ማንኛውም የመገናኛ ዘዴ እንዲዘጋ ወይም ደግሞ እንዲቋረጥ ሊያደርግ ይችላል፣ የአደባባይ ሰልፍ፣ መደራጀት እና በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስን ይከለክላል። ።” ብለዋል - የኮማንድ ፖስት ሰብሳቢው አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ።
በተጨማሪም፤ “ወንጀል ተፈፅሟል ብሎ ሲያምን በማንኛውም ጊዜና ሰዓት ከፍርድ ቤት ትዕዛው ውጪ ፍተሻ ማድረግ፣ ማስቆማና መበርበር ይችላል” ተብሏል።
አቶ ሲራጅ ከመግለጫው በኋላ የተወሰኑ ጥያቄዎችን ከጋዜጠኞች የተቀበሉ ሲሆን፤ በጥያቄና መልሱ የመንቅለ መንግሥት ሁኔታ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል አይኖርም ብለዋል።
የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ሐሳብ ስለሚያቀርቡ አካላት ተተይቀው፤”አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በሕዝብ የተመረጠ በመሆኑ የሽግግር መንግሥት መቋቋም አያስፈልግም” ብለዋል።
መርማሪ ቦርድ እንደሚቋቋም፣ የሰዓት እላፊ ተፈፃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ እንደሚወሰን ገልፀው፣ “የዐዋጁ ዝርዝሩ በመመሪያ ይወጣል” ብለዋል።
ዐዋጁን እንደገና ማራዘም ካስፈለገም ፓርላማው ሁኔታውን ገምግሞ ለአራት ወራት በድጋሚ ሊያራዝመው እንደሚችል አስታውቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG